ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ለአደጋ የተጋለጡ እና ብዙውን ጊዜ ለመብቶቻቸው መከበር የተለየ ድጋፍ እና ጥበቃ ካልተደረገ ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመዳረጋቸው ዕድል የሰፋ ነው
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የተሟላ መረጃ የያዘ እና በየጊዜው ወቅታዊ የሚደረግ የአመዘጋገብ ሂደት ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል
መንግሥት በኮንሶ ዞን እና በአጎራባች ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተደራጀ የምዝገባ ሥርዓት ማከናወን፣ የወሳኝ ኩነት አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ሰነዶችን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ፣ እንዲሁም በክልሉ ለተደጋጋሚ መፈናቀል መንስዔ ለሆኑ ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያፈላልግ ይገባል
“We are pleading with the IOM and other organizations to allocate funds and resources,” Tarikua Getachew said.
በካምፓላ ስምምነት ውስጥ የተካተቱ እና እንደ የሰነድና ምዝገባ፣ የጸጥታና ደኅንነት፣ የመንቀሳቀስ ነጻነት እና ፍትሕ የማግኘት መብት የመሳሰሉ መብቶችን እና በመንግሥት ላይ የተጣሉ ግዴታዎች ዙሪያ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ማሻሻል ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ባለፈው ዓመት ባደረጉት ጣምራ ምርመራበትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ጦርነት በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ እና የጦር ወንጀል ሊባሉ የሚችሉ የወንጀል ዓይነቶች መፈፀማቸውን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች መገኘታቸውን አመልክተው ነበር
አርብ ነሐሴ 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙት አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች የነበሩ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመር እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በበጎ እንደሚቀበለው ገልጸዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን 9 ሺህ እንደሚሆኑ የገመታቸው፤ የአፋር ክልል ደግሞ 7 ሺህ 800 ናቸው የሚላቸው የትግራይ ተወላጆች መመለስ የጀመሩት በዚህ ሣምንት ነው
ኢሰመኮ ሰኔ ወር ላይ ባወጣው መግለጫ በሁለቱ ካምፖች የሚገኙት ነዋሪዎች የትግራይ ክልል አዋሳኝ ከሆኑ ከአባአላ፣ ከኮነባና ከበረሃሌ የተሰኙ ሦስት የአፋር ክልል ወረዳዎች የመጡ መሆናቸውን አስታውቆ ነበር
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “ህገወጥና የዘፈቀደ እሥራት” ሲል በጠራው ሁኔታ አፋር ክልል ውስጥ ሰመራ አጋቲና ውስጥ ተይዘው የቆዩ የትግራይ ተወላጆች ተለቅቀው ወደ አብአላና ሌሎችም የቀድሞ መኖሪያ አካባቢዎቻቸው መመለስ መጀመራቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ