ከኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጋር የተደረገ ቆይታ
በሁለቱ ክልሎች ከተራዘሙ የትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው የሕግ ማስከበርና የመንግሥት መዋቅር መላላት ምክንያት በሰላማዊ ሰዎች ላይ በታጣቂ ኃይሎች፣ ለዘረፋ በተደራጁ ቡድኖችና በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አባሎች የሚፈጸሙ እገታዎች ተባብሰውና ተስፋፍተው መቀጠላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል ኮሚሽኑ
በአገሪቱ የሕግና ሥርዐት አለመከበርና የመንግሥት ሀገርን አረጋግቶ የመምራት ሂደት አለመቻል ሥርዐት አልበኝነትን እያነገሰ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል
ኢሰመኮ ባወጣው ሪፖርት እገታዎቹው ለዘረፋ "በተደራጁ ቡድኖች እንዲሁም በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት" የሚፈጸሙ ናቸው ብሏል
ወንጀሉ በአብዛኛው እንደ ገቢ ማስገኛ የተወሰደ መሆኑን የሚጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ድርጊቱ "በተደጋጋሚ፣ በተንሰራፋና በተደራጀ መልኩ እንደሚፈጸም፤ አልፎ አልፎም እንደ በቀል፣ ለፖለቲካ ዓላማ ወይም የታገተ ሌላ ሰውን ለማስለቀቅ በሚል በአጸፋ መልኩ የሚፈጸም መሆኑን" ስለመረዳቱ አመልክቷል