ዜጎችን ከመደበኛ የመኖሪያ ቦታቸው ያፈናቀሉ፣ የሰው ሕይወት ያጠፉ፣ ሀብት ያወደሙ፣ አካላዊ ጉዳት ያደረሱ ቡድኖችና ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ በቂ ዕርምጃዎች ባለመወሰዳቸው የሕግ በላይነት፣ ተጠያቂነትንና የተፈናቃዮችን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚነፍግ ነው ሲል፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
መንግሥት ለተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ የሚሰጥና የሚያስተባብር በግልጽ ሥልጣን የተሰጠው ተቋም በማቋቋም ወደ ሥራ ማስገባት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው
The decrease in humanitarian assistance has worsened the already dire humanitarian situation for host communities and IDPs
ለተፈናቃዮችና ተፈናቃይ ተቀባይ ማኅበረሰቦች ሲቀርብ የነበረው ሰብአዊ እርዳታ መቀነሱ ሰብአዊ ቀውስ እንዲባባስ አድርጓል
ሚሊዮን ዜጎቿ ተፈናቅለው የችግርና የሰቀቀን ኑሮ እየገፉ ቢሆንም የእነሱን ጉዳይ ጉዳዬ ብሎ የሚሰራ ተቋም የትኛው ነው ብላችሁ ብትፈልጉ አታገኙም