ለተፈናቃዮች የሚቀርበው ሰብአዊ ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን እና የጾታዊ ጥቃት ሥጋቶች መበራከታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ
ኢሰመኮ በኢትዮጵያ ካሉት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መካከል 2.2 ሚልዮን ያህሉ በግጭትና ጦርነት የተፈናቀሉ መሆኑን ለአሻም ገለጸ
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚኖሩባቸው ጣቢያዎች “ተገቢ ጥበቃ ስለማይደረግላቸው”፤ የታጠቁ አካላት “ሰርገው በመግባት ጥቃት እንደሚፈጽሙ” የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
በኢትዮጵያ ለተፈናቃዮች የሚደረጉ የሰብአዊ ድጋፍ እና ጥበቃ እንዲሁም የዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ ሥራዎችን የሚያስተባብር እና በበላይነት የሚመራ ተቋም ባለመኖሩ፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ አሳሳቢ ችግር ሆኖ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሁኔታን አስመልክቶ ባወጣው ሦስተኛ ዙር ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ውስጥ 56 በመቶ የሚሆኑት ከ1 ዓመት፤ 23 በመቶ የሚሆኑት ከ2 እስከ 4 ዓመት እና 11 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከ5 ዓመት በላይ በተራዘመ የመፈናቀል ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ብሏል
በኢትዮጵያ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የሚደርስ መፈናቀል እየተስፋፋ በመምጣቱ ይህን መሰል ሥጋት ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት እና በጉዳቱ ልክ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል
ዘላቂ መፍትሔ እስኪረጋገጥ ድረስ ተፈናቃዮች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ተደራሽ የሆነ የሰብአዊ ድጋፍ ሊቀርብላቸው እንዲሁም በቂ መጠለያ ሊመቻችላቸው ይገባል
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች፥ በቂ፣ ተደራሽ እና ወቅቱን የጠበቀ የምግብ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የተሟላ እና በቂ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ቢኖርም፣ ባለፉት ወራት በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ላሉ ተፈናቃዮች ትኩረት በመስጠት በሁለት ዙር ድጋፍ ማድረጉን ተናግሯል ተብሏል
የተፈናቀሉ ሰዎች ከመንግሥት አካላት ጥበቃ እና ሰብአዊ ድጋፍ የመጠየቅ እና የማግኘት መብት አላቸው። ይህን ጥያቄ በማቅረባቸው ሊከሰሱ ወይም ሊቀጡ አይገባም