«ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ባደረሱበት ከተማ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ቤትለቤት እየዞሩ በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ለይተው ገድለዋል» በማለት የምርመራ ግኝቱ ጠቁሟል
ኮሚሽኑ ያወጣው የምርመራ ዘገባ እንደሚያሳየው ከተገደሉት ሰዎች መካከል 42ቱ በተፈናቃዮች የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እና ከተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ ተፈናቃዮች እንዲሁም መንግሥትን ይደግፋሉ የተባሉ ነዋሪዎች ነበሩ