ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ እንዲሁም በመጠለያ ጣቢያዎች በቂ ምግብ፣ ውሃ፣ መጠለያ እና የጤና አገልግሎቶች እንዲቀርቡላቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን፣ በቆላ ሻራ ቀበሌ ውስጥ የደረሰውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሁኔታ በሚመለከት ከነሐሴ 22 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በአካባቢው በመገኘት ያደረገውን ምርመራ ይፋ አድርጓል
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ከአስተዳደራዊ መዋቅር ጋር ለተያያዙ አለመግባባቶች አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈለግ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ
በነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም. በቆላ ሻራ ቀበሌ ለደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነት ማረጋገጥ እና ከኃይል እርምጃዎች መቆጠብን ጨምሮ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ ማስጀመር እና በሀገራዊ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብት ሊረጋገጥ ይገባል
በተለያዩ አካባቢዎች ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መልሰው ስላልተቋቋሙ በተራዘመ የመፈናቀል አውድ ውስጥ ዓመታትን ለማሳለፍ ተገደዋል
በአዲስ መልኩ በሚዋቀሩ አካባቢዎች የሚነሱ የደመወዝ እና ተያያዥ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት በጤና እና በትምህርት መብት እንዲሁም በአካባቢዎቹ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሉ ሥጋቶችን ይቀርፋል