በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል
ውድድሩ በሽግግር ፍትሕ ሂደት ታሳቢ ሊደረጉ በሚገቡ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን 81 ትምህርት ቤቶች ተሳታፊ ሆነዋል
የወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ማዳበር በሽግግር ፍትሕ ሂደት አወንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ያግዛል
ሁሉም የሰው ልጆች እኩል ክብርና መብቶች ይዘው ነጻ ሆነው ተፈጥረዋል
All human beings are born free and equal in dignity and rights
የዚህ ዓመት ውድድር ምናባዊ ጉዳይ “በሽግግር ፍትሕ ሂደት በሚነሱ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች” ላይ ያተኩራል
States Parties shall take all appropriate measures with a view to achieving the full realization of every child’s right to education and shall in particular take measures to encourage regular attendance at schools and the reduction of drop-out rate
አባል ሀገራት የሕፃናትን የመማር መብት ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ ሁሉንም ተገቢ እርምጃዎች ይወስዳሉ። በተለይም በትምህርት ቤት ተገኝቶ ትምህርትን በቋሚነት መከታተልን ለማበረታታት እንዲሁም የተማሪዎችን ትምህርት የማቋረጥ ምጣኔ ለመቀነስ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው
ማንኛውም ሰው የግል ሕይወቱ፣ ግላዊነቱ፣ የመከበር መብት አለው። ይህ መብት መኖሪያ ቤቱ፣ ሰውነቱና ንብረቱ ከመመርመር እንዲሁም በግል ይዞታው ያለ ንብረት ከመያዝ የመጠበቅ መብትን ያካትታል
Everyone has the right to privacy. This right shall include the right not to be subjected to searches of his home, person or property, or the seizure of any property under his personal possession