የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ እና ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ከየካቲት 14 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በተለያዩ አካላት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በማድረግ ያዘጋጀውን ባለ 40 ገጽ ሪፖርት። የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች (Executive Summary) እዚህ ተያይዟል
ኢሰመኮ የፌዴራል ፣ የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች መንግሥታት በአፋጣኝ ሊተገብሯቸው ይገባል ካላቸው መካከል አንዱ በመረጃና በምዝገባ ሥርዓት የታገዘ፣ አሳታፊ የሆነ፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የተዘረጋለት እንዲሁም ከፍላጎት ጋር የተመጣጠነ ምላሽ ማቅረብ፣ ማሰራጨት እና ክትትል ማድረግ የሚለው ነው
ተሳታፊዎቹ ኮሚሽኑ ክትትል ሥራውን ማካሄዱን በበጎ እንደሚቀበሉት ገልጸው በክትትሉ ወቅት የታዩ ክፍተቶችን በመፍታት ረገድ ለሚመለከታቸው አካላት የውትወታ ሥራ በመስራት እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያዘጋጀው የዲሞክራሲ ተቋማት የሆኑት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ የፌደራል ኦዲተርና የመገናኛ ብዙኃን የማሻሻያ የለውጥ ስራዎችን የተመለከተ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
ይህ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ የሥራ ክፍሎቹ እና ጽ/ቤቶቹ አማካኝነት ባደረገው ክትትልና ምርመራ፣ ባከናወናቸው መለስተኛ ጥናቶች፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ ባካሄዳቸው ምርመራዎች፣ በውትወታ እና በሌሎች ተግባራቶቹ አማካኝነት ከተገኙ መረጃዎች የተዘጋጀ ነው። ሙሉ ሪፖርቱ...
የብሔራዊ ምርመራ ህዝባዊ የአቤቱታ ቅበላ ዘዴን ማካሄድ የሚያስችል አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
ሪፖርቱ የሚሸፍነው ጊዜ በኢትዮጵያ የበጀት ዓመት አቆጣጠር መሰረት ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ያሉትን 12 ወራት ሲሆን፣ በዓመቱ ውስጥ የነበረውን አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን፣ የተገኙ ቁልፍ እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ ተግዳሮቶችን እና ምክረ-ሃሳቦችን ያካትታል። የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች እዚህ ተያይዟል
The Ethiopian Human Rights Commission has published a detailed report on human rights violations over the past year. According to the findings, the country has suffered its worst record of rights violations as conflicts result in a surge of civilian killings
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በ2014 በጀት ዓመት የተከናወኑ የሰብዓዊ መብት ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል
The report covers the period between June 2021 and June 2022 (Ethiopian fiscal year) and consists of an overall assessment of the human rights situation in the country; key positive developments, main concerns, challenges and recommendations