በኢትዮጵያ የግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አምስት ክልሎች ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የታጠቁ ሰዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳወቀ። ኢሰመኮ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እሥራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታና የሀገር ውስጥ መፈናቀል እሳሳቢ መሆናቸውን ጠቅሷል
በግጭት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም በማድረግ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያፈላልጉም ኮሚሽኑ በድጋሚ ጠይቋል
በኢትዮጵያ በግጭት ዐውድ ውስጥ ያሉ አካባቢዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ
ይህ የሩብ ዓመት ሪፖርት በኢትዮጵያ የበጀት ዓመት አቆጣጠር መሠረት ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ መስከረም ወር 2017 ዓ.ም. መጀመሪያ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ቢሆንም የተወሰኑት ሁኔታዎች ቀደም ባሉት ወራት የተከሰቱና የቀጣይነት ባሕርይ ያላቸው ናቸው። በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፣ ሥጋቶች እና አሳሳቢ ሁኔታዎች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ይህ የሩብ ዓመት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተለይ በግጭት...
ከኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጋር የተደረገ ቆይታ
በተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ረገድ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እና አሠራሮችን የማሻሻል ተግባራትን ማጠናከር ያስፈልጋል
በሁለቱ ክልሎች ከተራዘሙ የትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው የሕግ ማስከበርና የመንግሥት መዋቅር መላላት ምክንያት በሰላማዊ ሰዎች ላይ በታጣቂ ኃይሎች፣ ለዘረፋ በተደራጁ ቡድኖችና በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አባሎች የሚፈጸሙ እገታዎች ተባብሰውና ተስፋፍተው መቀጠላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል ኮሚሽኑ
በአገሪቱ የሕግና ሥርዐት አለመከበርና የመንግሥት ሀገርን አረጋግቶ የመምራት ሂደት አለመቻል ሥርዐት አልበኝነትን እያነገሰ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል
ኢሰመኮ ባወጣው ሪፖርት እገታዎቹው ለዘረፋ "በተደራጁ ቡድኖች እንዲሁም በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት" የሚፈጸሙ ናቸው ብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እገታዎች በአሳሳቢ ሁኔታ መባባሳቸውን አስታውቆ መንግሥት ውጤታማ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠየቀ