Every woman shall be entitled to respect for her life and the integrity and security of her person. All forms of exploitation, cruel, inhuman or degrading punishment and treatment shall be prohibited
ማንኛዋም ሴት ለሕይወቷ እና ለአካል ደኅንነቷ ክብር የማግኘት መብት አላት፡፡ ሁሉም ዐይነት ብዝበዛ፣ ጨካኝ፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም ክብርን የሚያዋርድ ቅጣት እና አያያዝ የተከለከለ ነው
የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት በሕፃናት መሠረታዊ መብቶች የተቃኙ የእንክብካቤ፣ አገልግሎቶችና የጥበቃ ሥርዓቶች ሊኖራቸው ይገባል
The collective efforts of international, continental, and national institutions are essential to safeguard and promote children's rights across the African continent
ሁሉም ሕፃናት በሕይወት የመኖር፣ ወላጆቻችውን ወይም በሕግ የማሳደግ መብት ያላቸውን ሰዎች የማወቅና የእርነሱንም እንክብካቤ የማግኘት መብቶች አሏቸው
Every child has the right to life, to know and be cared for by his or her parents or legal guardians
States Parties which recognize the system of adoption shall ensure that the best interest of the child shall be the paramount consideration and establish a machinery to monitor the well-being of the adopted child
የጉዲፈቻ ሥርዓትን የተቀበሉ አባል ሀገራት የሕፃኑ ጥቅም ከሁሉም በላይ ቅድሚያ  የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው እንዲሁም የጉዲፈቻ ልጁን ደኅንነት ለመከታተል የሚያስችል አሠራር መዘርጋት አለባቸው
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር ያስፈልጋል