በመንግሥታዊም ሆነ በግል የማኅበራዊ ደኅንነት ተቋማት፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዳደር ባለሥልጣኖች ወይም በሕግ አውጪ አካላት በሚወሰዱ ማናቸውም ሕፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች የሕፃናት ደኅንነትና ጥቅም በቀዳሚነት መታሰብ አለበት
ሰፋፊ የእርሻ ልማቶች የሠራተኞቻቸውን በተለይም የሴቶች እና የወጣት ሠራተኞችን ሰብአዊ መብቶች ከማስጠበቅ አንጻር ኃላፊነት አለባቸው
የአፋር ክልል ረቂቅ የቤተሰብ ሕግ ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች አንጻር ተቃኝቶ ሊጸድቅ ይገባል
በዚህ ሳምንት የአንድ ለአንድ ዝግጅት በአሳሳቢው የሴቶች ጥቃት ላይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ እንግዳ አድርጓል
ግርዛት በሴቶች እና በሕፃናት ላይ የሚያደርሰውን አካላዊ እና ሥነልቦናዊ ጉዳት ለማስቀረት የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል
ከነበሩበት ቀዩ ለቀው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከገቡም በኃላ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚፈጸምባቸው ኢሰመኮ ጠቅሷል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በቀጠሉ ግጭቶችና የተፈጥሮ አደጋዎች ከ5ሺሕ የሚልቁ ትምሕር ቤቶች ተዘግተው የመማር ማስተማር ሂደቱ መቋረጡን በጥናት ማረጋገጡን አስታወቀ
ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው አንድ ዓመት በተሰበሰበ መረጃ በጅማ ከተማ ብቻ ከ50 በላይ ሕፃናት ተጥለው ተገኝተዋል
የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በሴቶች እና በሕፃናት የሰብአዊ መብቶች ላይ በተፈጸሙ ጥሰቶች እንዲሁም በሕግና ተቋማዊ የአሠራር ክፍተቶች ረገድ የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን በመተግበር ለሴቶች እና ሕፃናት መብቶች የተሻለ ጥበቃ ሊያደርጉ ይገባል
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የሴቶች እና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። ይህ የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተጨማሪነት የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ በዝርዝር በማተኮር በበጀት...