Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ለኢሰመኮ በአዲስ አበባ የሚቀርቡ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታዎች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ከአጋር አካላት ጋር የቅብብሎሽ አሠራር መፍጠር የሚያስችል ማዕቀፍ ስለመዘርጋቱ

August 22, 2022August 28, 2023 Event Update

የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል ለሚባሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች ነፃ የሕግ ድጋፍ፤ የመጠለያ፣ የጤና፣ የማኅበራዊና የሥነልቦናዊ አገልግሎት በመስጠት የሰብአዊ አገልግሎቱን የተሟላ ለማድረግ ያስችላል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሰብአዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው አቤቱታ አቅራቢዎች የተለያዩ የሕግ፣ ማኅበራዊና ሥነልቦናዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን በተሟላ መልኩ ማግኘት የሚችሉበትን እና በፌዴራልና ድሬዳዋ ማረሚያ ቤቶች ከእናቶቻቸው ጋር በእስር ላይ ለሚገኙ ሕፃናት የቅብብሎሽ ሥርዓት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመዘርጋት በዘርፉ ከተሰማሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማትና ሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ስብሰባ አካሂዷል። 

ኢሰመኮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ቤቶች እና የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ላይ ባካሄደው የክትትልና ምርመራ ሥራ የተለያዩ ክፍተቶችን ለይቷል። በፖሊስ ጣቢያዎች የተጠርጣሪ ማቆያዎች ውስጥ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችና ማረሚያ ቤቶች ያሉ ታራሚዎች አያያዝ በተቋማት አቅም እጦት ምክንያት አለመሻሻል፣ አቅም የሌላቸው ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች ቃል ከመስጠታቸው በፊትም ሆነ በምርመራ ወቅት እንዲሁም የአመክሮ ጊዜ ጨርሰው ወይም የተለያየ የመብት ጥያቄዎች ማቅረብ ለሚፈልጉ ታራሚዎች ተገቢውን አግልግሎት ለመስጠት የሚታዩ ውስንነቶች ተጠቃሽ ናቸው።

በተጨማሪም በኮሚሽኑ ሥልጣን ስር ክትትል የሚደረግባቸው ጉዳዮችን እልባት ለመስጠት ነፃ የሕግ፣ ማኅበራዊና ስነልቦናዊ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያደርግ ሥርዓት ባለመኖሩ ምክንያት ተገቢውን አግልግሎት መስጠት አለመቻልና የማስማማትም ሆነ ማኅበራዊና ሥነልቦናዊ ድጋፍ አገልግሎቶች አለመኖር ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው ሰብአዊ መብቶች የማስከበር ሥራዎች ላይ ተግዳሮቶች ሆነው ይታያሉ።

ከአጋር አካላት ጋር የትብብር፣ የቅንጅት እና የቅብብሎሽ አሠራር መፍጠር ላይ ባተኮረው የውይይት መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕፃናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዳኛ ልዑለሥላሴ ሊበን፣ የፌዴራልና ድሬዳዋ ማረሚያ ቤቶች ምክትል ኮሚሽነር ሙላት አለሙና ኮሚሽነር ወንድሙ ጫማ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእስረኞች አስተዳደር ኃላፊ፣ የአዲስ አበባ ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሜሮን አራጋው እና የፍትሕ ሚኒስቴር ተወካዮችን ጨምሮ 55 የሚሆኑ በፍትሕ ዘርፉ የተሰማሩ መንግሥታዊ ተቋማት፤ የሕግ፣ ማኅበራዊና ሥነልቦናዊ ድጋፍ የሚሰጡ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመተባበርና በመቀናጀት የሚከናወን መሆኑን ገለጸዋል። አክለውም ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ጠብቀው ሰብአዊ መብቶችን እንዲያስከብሩ በተባበሩት መንግሥታት የፓሪስ መርሆች ውስጥ ከተቀመጡት መስፈርቶች መካከል አንዱ እንደሆነና ኮሚሽኑም በስትራቴጂክ ዕቅዱ ቁልፍ ተግባር አድርጎ እየሠራበት መሆኑን አመላክተዋል፡፡ የኢሰመኮ የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ በበኩላቸው ለወደፊቱ ወጥ የሆነ መደበኛ ሥርዓት የሚዘረጋው ቅብብሎሽ ሥርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ ይህን መጠበቅ ሳያስፈልግ ኢመደበኛ በሆነ መንገድ በመተባበር አገልግሎቱን በአፋጣኝ ለማስጀመር ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡

በስብሰባው ተሳታፊ የነበሩት የኬንያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባልደረባ ጆሴፍ ኦቲዬኖ፣ የማኅበራዊና ሥነልቦና ድጋፍ አገልግሎት በቅንጅት የሚሰጥበትን አሠራር አስመልክቶ የኬንያን ተሞክሮ ለተሳታፊዎች አጋርተዋል። በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕፃናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዳኛ ልዑለሥላሴ ሊበን ሕፃናት ተጠቂ ወይም ምስክር እንዲሁም በወንጀል ተግባር ተሳታፊ ሆነው እንዲሁም በወላጆች መካከል በሚከሰት አለመግባባት ምክንያት ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሕፃናትን ጥቅምና ደኅንነት (best interest of the child) ለማስጠበቅ በትግበራ ላይ ያሉ የቅብብሎሽና የትብብር ሥራዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ የሴቶችና ሕፃናት ቢሮ በከተማው በሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተማዎች በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሰረት ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትና የፓራ ሌጋል (Para Legal) ባለሙያዎች በተጠናከረ መንገድ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሜሮን አራጋው ተናግረዋል። አክለውም ይህ አገልግሎት ኢሰመኮ ካለው ፍላጎት ጋር ተመጋጋቢ በመሆኑ ተቀናጅቶ መሥራት እንደሚቻልና በስብሰባው የተገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከቢሮው ጋር በተፈራረሙት የትግበራ ስምምነት መሰረት አገልግሎት በመስጠት የተቋቋሙለትን ኃላፊነት ለመወጣት ኮሚሽኑ ለሚልካቸው ተጎጂዎች አገልግሎት መስጠት መጀመር የሚቻል መሆኑን አስረድተዋል።

የኢሰመኮ የክትትልና ምርመራ ሥራ ክፍል ከፍተኛ ዳይሬክተር የሆኑት ይበቃል ግዛው ባሰሙት የማጠቃለያ ንግግር፣ ኮሚሽኑ ሊዘረጋው በዝግጅት ምዕራፍ ላይ ለሚገኘው የቅንጅት፣ የትብብር እና የቅብብሎሽ ሥርዓት በቂ ግብዓት መሰብሰብ የተቻለበትና የአጋር አካላት ዝግጁነትን ለመገንዘብ ዕድል የተገኘበት መሆኑን አመላክተዋል፡፡

Related posts

November 19, 2022November 21, 2022 Event Update
በአፋር ክልል ለሚቀርቡ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታዎች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ከአጋር አካላት ጋር የቅብብሎሽ አሠራር መፍጠር የሚያስችል ማዕቀፍ መዘርጋቱ ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ የላቀ አስተዋጾ አለው
October 17, 2022October 18, 2022 Event Update
በሶማሌ ክልል በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎችን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ለማሻሻል ባለድርሻ አካላት የተጀመሩ ጥረቶችን ሊደግፉ ይገባል
October 31, 2023November 7, 2023 Event Update
በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሂደት ውስጥ የጥቃት ተጎጂ የሆኑ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች መከበር ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
June 15, 2023August 28, 2023 Event Update
ጋምቤላ:- የታራሚዎችና የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ለማሻሻል የፍትሕ አካላት ቅንጅትን ይጠይቃል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.