Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በግሉ የጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለሕብረተሰቡ በፋይናንስ ተደራሽ እንዲሆኑ የአሠራር፣ የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያ ያስፈልጋል

June 9, 2023August 28, 2023 Press Release, Report

የጤና መብትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ እና የመንግሥት አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Download Download Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የግሉ የጤና ዘርፍ ከሕብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም ጋር የተመጣጠነ እና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት አቅርቦት ላይ ያተኮረ ባለ 39 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የጤና መብት ተገኝነት፣ ተደራሽነት፣ ተቀባይነት እና ጥራት ላይ ያተኮሩ አራት ዋና ዋና ይዘቶች ያሉት ሲሆን ክትትሉ በተደራሽነት (accessibility) ሥር ከተጠቃለሉት ንዑስ ይዘቶች መካከል በገንዘብ ተደራሽነት ላይ ትኩረት በማድረግ መከናወኑ በሪፖርቱ ተብራርቷል። ሪፖርቱን ለማዘጋጀት በአጠቃላይ ከ218 የባለድርሻ አካላት (80 የግል የጤና ተቋማት ኀላፊዎች፣ 8 መንግሥታዊ ያልሆኑ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ተጠሪዎች፣ 20 የመንግሥት ተቋማት ኀላፊዎች፣ 80 የግል የጤና ተቋማት ተጠቃሚዎች/ተገልጋዮች እና 30 የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች) ከሃዋሳ፣ ከባሕር ዳር፣ ከአዲስ አበባ እና ከጅማ ከተሞች መረጃዎች ተሰብስበዋል።

የግሉ የጤና ዘርፍ አገልግሎት ከመንግሥት የጤና ዘርፍ አገልግሎት አንጻር ሲታይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሕብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም በላይ እየሆነ መምጣቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ለዚህም ዋነኛ ምክንያቶች የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦት እጥረት እና ዋጋ መናር፣ የግዴታ ግዥ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት እና ቁጥጥር አናሳ መሆን፣ ከሙያ ሥነ ምግባር ውጪ የሆኑ ተግባራት እና በመንግሥት ተቋማት የተሟላ እና አመርቂ አገልግሎት አለመኖር መሆናቸው ተጠቅሰዋል።

ኢሰመኮ የጤና መብት በተሻለ ሁኔታ እንዲተገበር እና ከላይ የተዘረዘሩትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ይረዳሉ በማለት የለያቸውን የአሠራር፣ የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያ ምክረ ሐሳቦችን በሪፖርቱ አቅርቧል። ከእነዚህም መካከል በሕዝብ የጤና ተቋማት ላይ የአገልግሎት እና የአቅርቦት ማሻሻያ እና ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ሕብረተሰቡ አማራጭ እንዲያገኝ ማድረግ፣ መሠረታዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የጤና መድኅን አገልግሎት ማስፋፋት እና የግል የጤና ተቋማትም የሚሳተፉበትን አሠራር መዘርጋት፣ የመንግሥት እና የግል የጤና ተቋማት ሽርክናዎችን (public-private partnerships) ማጠናከር የሚሉት በምክረ ሐሳብነት በሪፖርቱ ተካተዋል።

በተጨማሪም ለሕግ ባለሞያዎች ተግባራዊ የተደረገውን ነጻ የሕግ አገልግሎት (pro bono legal service) ተሞክሮ ላይ በመመሥረት በግል ዘርፍ የተሰማሩ የጤና ባለሙያዎች በሰዓት የተገደበ ነጻ የሕክምና ሙያዊ አገልግሎት (pro bono medical service) እና የግል የጤና ተቋማቱም በየደረጃቸው ዝቅተኛው መጠን የተወሰነ ድርጅታዊ ማኅበራዊ ኅላፊነት በነጻ ለማኅበረሰቡ እንዲሰጡ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት እና የፋይናንስ ተቋማት ለግል የጤና ተቋማት በአነስተኛ ወለድ እና የሕክምና መሣሪያዎችን በመያዣነት በመጠቀም ብድር የሚሰጡበትን ሁኔታ ማመቻቸት የሚሉት በሪፖርቱ በዝርዝር ተገልጸዋል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአብዛኛው በመንግሥት ሲቀርብ በነበረው የጤና አገልግሎት ላይ የግሉ ዘርፍ በሰፊው መሰማራቱ ሊበረታታ እንደሚገባው ገልጸው ተቋማቱ ካላቸው የፋይናንስ ተደራሽነት አንጻር ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ አስረድተዋል። ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም የግል የጤና ተቋማት ለሕብረተሰቡ በገንዘብ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማስቻል እና የጤና መብትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ግዴታ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሙሉ ሪፖርቱ እዚህ ተያይዟል
አንኳር ጉዳዮች

Related posts

June 6, 2023August 28, 2023 Press Release
የአካል ጉዳተኞችን ትምህርት የማግኘት መብት ለማረጋገጥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እና አካታች ሊሆኑ ይገባል
May 19, 2023August 28, 2023 Event Update
ኢሰመኮ የግል የጤና ተቋማት የፋይናንስ ተደራሽነት እና የጤና መብት አተገባበር ሁኔታን በተመለከተ ባከናወነው ክትትል ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ
May 12, 2023May 15, 2023 Event Update
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ ለሚያልፉ ሰዎች የሚሰጠው ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ማሻሻል
September 6, 2023September 6, 2023 Press Release
የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶችን በተመለከተ አስቻይ የሕግ እና ተቋማዊ ማእቀፎች ሊቀረጹ ይገባል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.