Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

አዲስ አበባ፦ ምግብ የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ የምገባ መርኃ ግብሮች ሚና እና ሰብአዊ መብቶች ተኮር አቀራረብ

May 7, 2024May 7, 2024 Event Update

ምግብ የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ እና ሰብአዊ መብቶች ተኮር ለማድረግ የመንግሥትን እና የባለድርሻዎችን ጥምር ጥረት ይጠይቃል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) “የምግብ መብት በኢትዮጵያ፤ የምገባ መርኃ ግብሮች የምግብ መብትን ለማሟላት ያላቸው ሚና እና የሰብአዊ መብቶች ተኮር አቀራረብን መከተላቸው” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምገባ መርኃ ግብሮች ላይ ትኩርት በማድረግ ባከናወነው ጥናት ላይ ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር  ውይይት አካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት፣ የሚመለከታቸው የሚኒስቴር እና የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች ተወካዮች እንዲሁም የምገባ መርኃ ግብሮቹ አካል የሆኑ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተሳትፈዋል። ጥናቱ የኢትዮጵያ የሕግ እና የፖሊሲ ማዕቀፎች ከዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ  የምግብ መብት ማዕቀፎች ጋር  የሚጣጣሙ መሆናቸውን  በመዳሰስ እና በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወኑ የትምህርት ቤት እና የተስፋ ብርሃን ማእከላት የምገባ መርኃ ግብሮችን በሰብአዊ መብቶች ተኮር አቀራረብ በመገምገም የተከናወነ ነው፡፡

የምግብ መብትን የተመለከቱ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ማዕቀፎች፣ የጥናቱ ግኝቶች እንዲሁም  ምክረ ሐሳቦች በዝግጅቱ ወቅት ለተሳታፊዎች ቀርበዋል። በተመሳሳይ  ለጥናቱ ግብአት የሆኑ መረጃዎችን የማሰባሰብ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ በተፈጠሩ አዳዲስ ጉዳዮች ላይ ከተሳታፊዎች አስተያየቶች ተሰብስቧል፡፡ በተጨማሪም በጥናቱ የተለዩ ክፍተቶች እንዲስተካከሉ እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች እንዲተገበሩ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ዙሪያ ባለድርሻ አካላቱ ሰፊ ውይይትና ምክክር አድርገዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በጥናቱ የተለዩ ክፍተቶች እና የቀረቡ ምክረ ሐሳቦች የምግብ መብት ትግበራ ችግርና ነባራዊ ሁኔታውን የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። አክለውም በኢትዮጵያ የመብቱ ጥሰት መንስኤዎች እንዲቀረፉ ኮሚሽኑ ተጨማሪ ውትወታዎችን እንዲያደረግና በጥናቱ የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች እንዲፈጸሙ በቅርበት እንዲከታተል ጠይቀዋል።

የኢሰመኮ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል በውይይቱ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፤ “ከዐቅማቸው በላይ በሆነ ምክንያት የምግብ  ፍላጎታቸውን ማሟላት ለማይችሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች መንግሥት የተለያዩ መርኃ ግብሮችን በሰብአዊ መብቶች ዘዴዎች በመቅረጽና በመተግበር ምግብ የማግኘት መብትን የማረጋገጥ ግዴታውን እንዲወጣ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዎጽዖ ማድረግ አለባቸው” ብለዋል። አክለውም በመድረኩ የተሰጡ ተጨማሪ ግብአቶችን በማካተት በክትትሉ የቀረቡ ምክረ ሐሳቦች ሙሉ ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ የውትወታ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

Related posts

January 3, 2024January 3, 2024 Event Update
ምግብ በማግኘት መብት እና ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ አቀራረብ ላይ የተሰጠ ስልጠና
October 18, 2023October 23, 2023 Event Update
በምግብ ሥርዓት፣ ምግብ የማግኘት መብት እና ሰብአዊ መብትን መሠረት ያደረገ አቀራረብ ዙሪያ የተካሄዱ ስልጠናዎች
May 19, 2023August 28, 2023 Event Update
ኢሰመኮ የግል የጤና ተቋማት የፋይናንስ ተደራሽነት እና የጤና መብት አተገባበር ሁኔታን በተመለከተ ባከናወነው ክትትል ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ
April 18, 2023April 18, 2023 Event Update
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጎጂዎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ካሳ እና የሚተገበሩ የመፍትሔ አማራጮች የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ይጠይቃሉ

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.