
የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ በማረሚያ ቤቶች ላይ የሰብአዊ መብቶች አከባበር እና አጠባበቅ፤ የኑሮ ሁኔታ እንዲሁም ከቀለብ ጋር በተያያዘ በክትትል መምሪያ ዳይሮክተሬት በኩል በየጊዜው ክትትል ያደርጋል። በክትትል ሂደቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚበረታቱ ለውጦች ቢኖሩም ከቀለብ እና ከበጀት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች ትኩረት ሊሰጥባቸው ይገባል ብለዋል