Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፡ የጤና መብት እና የግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበር ክትትል ሪፖርቶች ላይ የውትወታ መድረኮች ተካሄዱ

January 9, 2024April 10, 2024 Event Update

የጤና መብት እና በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት በተሻለ ሁኔታ እንዲተገበሩ ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሠሩና የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በግል የጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ለኅብረተሰቡ ያላቸው የፋይናንስ ተደራሽነትና የጤና መብት አተገባበር እና በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበር ዙሪያ በ2015 ዓ.ም. የሠራቸውን የክትትል ሪፖርቶች መሠረት በማድረግ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ታኅሣሥ 23 እና 24 ቀን 2016 ዓ.ም. የውትወታ መርኃ ግብሮችን አካሄደ። የመርኃ ግብሮቹ ዐላማ በክትትል ሪፖርቶቹ የተለዩ ግኝቶችን መሠረት በማድረግ የተሰጡትን ምክረ ሐሳቦች ለባለድርሻ አካላት በማስገንዘብ መብቶቹ በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆኑ ማስቻል ነው፡፡

የግል የጤና ተቋማት ለኅብረተሰቡ የፋይናንስ ተደራሽነታቸውንና የጤና መብት አተገባበርን አስመልክቶ በተካሄደው የውትወታ መርኃ ግብር ከክልሉ፤ የጤና ጥበቃ ቢሮ እና የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን፤ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ እና ጤና መድኅን ኤጀንሲ አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች፤ ከተለያዩ የግል ጤና ተቋማት፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና በጤና አገልግሎት ቁጥጥርና አቅርቦት ላይ ከሚሠሩ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የውትወታ መርኃ ግብሮቹ ተሳታፊዎች

በጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለኅብረተሰቡ ያላቸው የፋይናንስ ተደራሽነት እና የጤና መብት አተገባበር በሚመለከት በኮሚሽኑ የተደረገው የክትትል ሪፖርት ግኝቶች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ቀርበዋል፡፡ የግሉ የጤና ዘርፍ ለጤና አገልግሎት ዋጋ ንረት ያለው ሚና እና በዘርፉ የሚጠየቁ ክፍያዎች መጠን ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮች፣ ግለሰቦች በግል ተቋማት እንዲገለገሉ የሚያስገድዱ ምክንያቶች፣ ለግሉ የጤና ዘርፍ የመንግሥት ድጋፍ፣ ቁጥጥር እና ክትትል፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሻሻል የሚረዱ ተግባራት እና በዘርፉ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም የሚስተዋሉ ችግሮችን እንዴት መቅረፍ እንደሚቻል፣ በክትትል ሪፖርቱ የተለዩ ምክረ ሐሳቦች ስለሚተገበሩባቸው መንገዶች እና በቀጣይ ከእያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ስለሚጠበቁ ተግባራት አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዮሴፍ ሶንኮ፣ ጉዳዩ ሁሉንም የሚመለከት መሆኑን በመግለጽ የተለዩትን ክፍተቶች ለመሙላት ሁላችንም የየድርሻችንን በመወጣት የግል የጤና ተቋማት ለኅብረተሰቡ በገንዘብ ተደራሽ እንዲሆኑ በማስቻል የጤና መብትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ የግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበርን በተመለከት በተካሄደው የውትወታ መርኃ ግብር ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተውጣጡ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ዘርፍ፣ የግንባታ ዘርፍ አስፈጻሚ አካላት እና የግንባታ ተቋራጮች ተወካዮች ተሳትፈዋል። በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበርን በሚመለከት ኮሚሽኑ በአምስት ከተሞች ባካሄደው ክትትል የተለዩ ግኝቶች ማለትም ባለድርሻ አካላት ስለመብቱ ያላቸውን ግንዛቤ፣ የሥራ ደኅንነት እና ጤንነት መብት የአተገባበር ኃላፊነት ያለባቸው ተቋማት ተቋማዊ አደረጃጀት፣ የአደጋ ሥጋትን ወይም በጤና ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል እና ለማስቀረት በአሠሪዎች የሚወሰዱ እርምጃዎችን፣ በዘርፉ ያለውን የሠራተኛ ማኅበራት እና የሠራተኞች ተሳትፎ እንዲሁም ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ ሠራተኞች የሚደረግ ልዩ ጥበቃን የሚመለከቱ የክትትሉ ግኝቶች ተገልጸዋል። በተጨማሪም የሥራ ሁኔታ ክትትል፣ ቁጥጥር እና ድጋፍ ተግባራት፣ በዘርፉ በብዛት የሚስተዋሉ አደጋዎች፣ በሽታዎች እና ምክንያቶቹ፣ በዘርፉ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ መልካም ተሞክሮዎች እና ተስፋ ሰጪ ጅምሮች ተብራርተዋል።

የውትወታ መርኃ ግብሮቹ ተሳታፊዎች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌ ጤናማና ምቹ የሥራ ሁኔታን ለመፍጠር የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ በማሳደግ ተባብረን መሥራት አለብን ያሉ ሲሆን የግንባታ ተቋራጮችም ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በመረዳት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል። ተሳታፊዎች በበኩላቸው የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት በማድረግ በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበር ተግዳሮቶችን እና መልካም አጋጣሚዎችን በማንሳት ተወያይተዋል። በክትትል ሪፖርቱ የተለዩ ምክረ ሐሳቦች ስለሚተገበሩባቸው መንገዶች እና በቀጣይ ከእያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ምን እንደሚጠበቅ ያላቸውን አስተያየትም ሰጥተዋል።

የኢሰመኮ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል በጤና ዘርፍ ለሚሰጡ አገልግሎቶች የሚጠየቁ ከፍያዎች ከኅብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ በማድረግ ተደራሽነታቸውን ለማስፋት መንግሥትና የግሉ ጤና አገልግሎት ሰጪ አካላት በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት በተሻለ ሁኔታ እንዲተገበር የባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፡ የጤና መብት እና የግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበር ክትትል ሪፖርቶችን መሠረት ያደረጉ የውትወታ መድረኮች ተካሄዱ

Related posts

October 12, 2023August 8, 2024 Event Update
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፡- የጤና መብት እና የግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበር ክትትል ሪፖርቶችን መሠረት ያደረጉ የውትወታ መድረኮች ተካሄዱ
June 13, 2023August 28, 2023 Event Update
በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበር
July 7, 2023August 28, 2023 Press Release
በግንባታ የሥራ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታን ለማረጋገጥ የሕግና ፖሊሲ አተገባበሮችን ማሻሻል ያስፈልጋል
May 19, 2023August 28, 2023 Event Update
ኢሰመኮ የግል የጤና ተቋማት የፋይናንስ ተደራሽነት እና የጤና መብት አተገባበር ሁኔታን በተመለከተ ባከናወነው ክትትል ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.