Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ጥሩ ሥራና ደመወዝ (Decent Work and Wage)

April 29, 2024April 29, 2024 Explainer

ጥሩ ሥራ (Decent Work) ምን ማለት ነው? የጥሩ ሥራ መመዘኛዎቹ ምንድናቸው? ጥሩ ሥራን ማስጠበቅ ምን ዐይነት ጠቀሜታ ይኖሩታል?

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

ጥሩ ሥራ (Decent Work) ምን ማለት ነው?

ጥሩ ሥራ ማለት ውጤታማና በቂ የሆነ ገቢ የሚያስገኝ፣ የሥራ ላይ ዋስትናው የተጠበቀ፣ ለሠራተኛውና ለቤተሰቡ ማኅበራዊ ዋስትና የሚሰጥ፣ ሠራተኞች ያላቸውን ሐሳብ በነጻነት የሚገልጹበትና መብታቸው የሚከበርበት፣ በሕይወታቸው ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ውሳኔዎች ላይ የሚገኙበትና የሚሳተፉበት፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ አካባቢ ያለው እንዲሁም ሴቶችና ወንዶች በእኩልነት የሚስተናገዱበትና እኩል ዕድል የሚያገኙበት እንዲሁም በሠራተኞች መካከል በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጾታና በአካል ጉዳት ምክንያት አድልዎ የማይደረግበት ሥራ ነው። የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባሕል መብቶች ኮሚቴ የመሥራት መብት ላይ በሰጠው አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 18 ጥሩ ሥራ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብቶችን እንዲሁም ደመወዝና የሥራ ደኅንነት ሁኔታዎችን ጨምሮ የሠራተኞችን መብቶች ያከበረ ሥራ እንደሆነ ይገልጻል።

የጥሩ ሥራ ፅንሰ ሐሳብ የማይነጣጠሉ፣ የተያያዙ እና እርስ በእርስ የሚደጋገፉ የተለያዩ ዐምዶችን የያዘ ሲሆን እነዚህም፦ የሥራ ዕድል የማግኘት፣ የሥራ ላይ መብቶች፣ ማኅበራዊ ጥበቃ እና ማኅበራዊ ምክክርን ያጠቃልላል።

  • የሥራ ዕድል ማግኘት፡ የጥሩ ሥራ መገለጫ  አንዱ ባሕሪይ  ውጤታማ የሆነ የሥራና ደመወዝ የማግኘት ዕድል ለሁሉም ሰው ክፍት የሆነ፣ እኩል ተደራሽ እና ከአድልዎ የጻዳ መሆኑ ነው። የመሥራት መብት ፅንሰ ሐሳብም ማንኛውም ሰው ኑሮውን ለመምራት የሚያስችል የሥራ ዕድል የማግኘት እንዲሁም አላግባብ ሥራውን ያለመነፈግ መብትን ያካትታል።
    በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ተቀብላ ያጸደቀችው የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባሕል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን ተዋዋይ ሀገራት ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገትን የሚያስገኙ ምርታማ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያስችሉ እርምጃዎችን ሊወስዱ እንደሚገባ ያብራራል። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም ሰዎች ጠቃሚ ሥራ የማግኘት ዕድላቸው እየሰፋ እንዲሄድ ለማድረግ መንግሥት አስፈላጊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ይደነግጋል።
  • የሥራ ላይ መብቶች፡ የሠራተኞች ፍትሐዊና ምቹ የሥራ ሁኔታ የማግኘት፣ በተገደበ የሥራ ሰዓት የመሥራት፣ ከሥራ ላይ እረፍት ማግኘት፣ ከአድልዎ ነጻ የመሆን፣ ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ የማግኘት መብትን እንዲሁም ቤተሰብንና እራስን በቂ በሆነ የኑሮ ደረጃ ለማኖር የሚያስችል ደመወዝ የማግኘት መብትን ያካትታል። ስለሆነም ጥሩ ሥራ የግዳጅ ሥራን፣ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛን እንዲሁም በሥራ ቦታ የሚደረጉ ሁሉንም ዐይነት አድልዎን ማስወገድ አለበት። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም ለሴቶች የወሊድ እረፍት ከደመወዝ ጋር የማግኘት፣ ጤናማና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት እና ሕፃናት ከጉልበት ብዝበዛ የመጠበቅ መብቶችን ጨምሮ አጠቃላይ የሠራተኛ መብቶች መርሕን  ይደነግጋል።
  • ማኅበራዊ ጥበቃ (Social protection)፡ ሰዎች የተሰማሩበት ሥራ የአስቸኳይ ጊዜ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ከድንገተኛ ሁኔታዎች እንዲጠበቁ ለማድረግ የሚያስችል ሲሆን የጥሩ ሥራ  ሌላው መገለጫ ባሕሪይ ነው። ይህ ዐምድ በውስጡ ማኅበራዊ ዋስትናን፣ የሠራተኞች ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ፣ በቂ ነጻ ጊዜና እረፍት፣ የጤና እንክብካቤ፣ ለቤተሰብ ማኅበራዊ ጥበቃ እና እንደ ወላጅ እረፍት ያሉትንና የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ማግኘትን ያካትታል።
  • ማኅበራዊ ምክክር(social dialogue)፡ ከመንግሥት ተወካዮች፣ ከአሠሪዎች እና በሠራተኞች  መካከል ባሉ የጋራ ፍላጎቶች፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፖሊሲዎች ላይ የሚደረጉ ምክክሮች፣ ድርድሮች እና የሐሳብ ልውውጦችን ያካትታል።በዋነኝነት የሠራተኛውን መብት ለማስጠበቅ ከአሠሪዎችና ከመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ላይ ያተኩራል። በዘርፉ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ማኅበራዊ ፍትሕን የያዙ ፖሊሲዎችን ተፈጻሚ ለማድረግ ማኅበራዊ ምክክር ጥቅም ላይ ይውላል። ይህም የሠራተኛውን መብት ለማስከበርና የሥራ ላይ ዋስትናን ለማረጋገጥ አንዱ መንገድ ነው። በአጠቃላይ የሥራ ሁኔታን አስመልክቶ በአሠሪና በሠራተኛ፣ ስለ ተቋም አሠራር በአስተዳደርና በሠራተኛው፣ እንዲሁም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲን በተመለከተ በመንግሥት፣ በአሠሪና ሠራተኛው መካከል የሚደረግ ምክክር ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የመደራጀት መብት እንዲሁም ሥራ ማቆምን ጨምሮ ቅሬታን የማሰማት መብት ዕውቅና ይሰጣል።
  • የሥራ ቦታ ኅብረት ድርድር (collective labour bargaining) አንዱ ማኅበራዊ ምክክር የሚደረግበት መንገድ ነው። በኢትዮጵያ የኅብረት ድርድር ማድረግ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ግጭትን ለመፍታት፣ ማኅበራዊ ፍትሕን ለማስፈንና የፖሊሲ ውጤታማ አፈጻጸም ለማምጣት ጠቀሜታ ያለው መሆኑ ዕውቅና ተሰጥቶታል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (International Labour Organization- ILO) ስምምነት የሆኑትን የመሰብሰብ ነጻነትና የመደራጀት መብት ጥበቃ ስምምነት ቀጥር 87 እና የመደራጀትና የኅብረት ድርድር የማድረግ መብት ስምምነት ቁጥር 95 እንዲሁም የሦስትዮሽ ምክከር ስምምነት ቁጥር 144 አጽድቃለች።  

የጥሩ ሥራ መመዘኛዎቹ ምንድናቸው?

ሀ. ዋስትና ያለው መሆኑ

የጥሩ ሥራ አንዱ መመዘኛ ዋስትና ያለውና ቋሚ መሆኑ ነው። የሥራ ላይ ዋስትና ማለት ሠራተኛው  በሥራው ላይ መቀጠል እንደሚችል ማረጋገጥ ሲቻል ነው። ይህም የሠራተኛው የሥራ ውል ጊዜ ቆይታ፣ የሥራው ባሕሪ፣ ማኅበራዊ ደኅንነት እና ሌሎች ማኅበራዊ ጥቅሞች የማግኘት ሁኔታን በመገምገም ነው። የሥራ ውል በሕጋዊ መንገድ ሊቋረጥባቸው የሚችሉ ተገቢ ምክያቶችን አስቀድሞ በመዘርዘር እና አላግባብም ሲቋረጥ የሚያስከትለውን ውጤት በመግለጽ የሥራ ላይ ዋስትናን ማረጋገጥ ይቻላል።

በኢ-መደበኛ የሥራ ግንኙነት ላይ የተመሠረቱ ሥራዎች ደኅንነታቸው ያልተጠበቁና ክፍያቸው አነስተኛ በመሆኑ በአሠሪውም ሆነ በሠራተኛው በማንኛውም ጊዜ ሊቋርጡ ይችላሉ። በአብዛኛው ለእንደዚህ ዐይነት ሥራዎች (ሁኔታዎች) የሚጋለጡት የትርፍ ሰዓት ሥራ፣ የራስ ሥራ፣ ኢንተርኔትንና ስልክ በመጠቀም የሚሠራ ሥራን ጨምሮ በቤት ውስጥ የሚሠራ ሥራ፣ ጊዜያዊ፣ ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ እና አልፎ አልፎ በሚመጣ ሥራ ላይ የሚሰማሩ ሠራተኞች ናቸው። እነዚህ የሥራ ዐይነቶች በአብዛኛው የሥራ ዋስትናቸው ያልተረጋገጠ፣ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ እና ክፍያቸው አነስተኛ በመሆኑ መደበኛው የሥራ ግንኙነት ሁኔታ የሚያሟላውን መስፈርት የሚጎድላቸው ናቸው።

ለ. በሥራ ላይ በእኩልነት የመስተናገድና እኩል ዕድል የማግኘት መብት

በሥራ ላይ በእኩልነት የመስተናገድና እኩልዕድል የማግኘት መብት የጥሩ ሥራ አንዱ ገጽታ ነው። ይህ የሚያመላክተው ከሥራ ጋር ተያይዞ የሚደረግ ማንኛውም ዐይነት አድሏዊ ልዩነት ሊኖር እንደማይገባ ነው።  ከሠራተኛ አስተዳደር ጋር ተያይዥነት ያላቸው ፖሊሲዎች ሊተገበሩ የሚገባው ጾታዊ እኩልነትን በማበረታታት እንዲሁም በሠራተኞች ወይም ለሥራ ቅጥር በሚያመለክቱ ሰዎች መካከል ምንም ዐይነት አድልዎን ባለማድረግ ነው። በዚህ ላይ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባሕል መብቶች ኮሚቴ በሰጠው አጠቃላይ ትንታኔ ሀገራት በተለይ የተገለሉ ግለሰቦችና ቡድኖች፣ ሴቶችና ወጣቶች ጥሩ ሥራ የማግኘት መብታቸውን የማክበር እንዲሁም አድሎአዊ ልዩነትን የሚዋጉና እኩል ተደራሽነትና ዕድሎችን የሚያጎለብቱ እርምጃዎችን የመውሰድ ግዴታ እንዳለባቸው ያስገነዝባል።

ሐ. ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ አካባቢ

ሠራተኞች የአካልና የሥነ አእምሮ ጤናቸው ተጠብቆ ሊሠሩ ይገባል። የሥራ ቦታ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ጤናማና ከማንኛውም አደጋ የነጻ እንዲሆን አሠሪ አስፈላጊ እርምጃዎችን ሁሉ መውሰድ ይኖርበታል። የሠራተኛን የሥራ ላይ ደኅንነት ለማስጠበቅ ማንኛውም አሠሪ ሊወስዳቸው ስለሚገባ ዝርዝር የጥንቃቄ እርምጃዎች በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እንዲሁም የመንግሥት መሥሪያ ቤትን አስመልክቶ በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ተደንግጓል። ሠራተኛውም ይህን ለማሳካት የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎችን የማክበር፣ እንዲሁም የመተባበር ግዴታ አለበት።

ኢትዮጵያ የሥራ ላይ ደኅንነት፣ ጤና እና የሥራ አካባቢን አስመልክቶ የወጣውን የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ስምምነት ተቀብላለች። በዚህ ስምምነት የተቀመጡ መስፈርቶች እንዲሁም በአዋጆቹ የተደነገጉ ግዴታዎች በሀገር ደረጃ ብሎም በየተቋማቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር መሠረት የሚሆኑ ናቸው። ለአብነትም ስምምነቱ በተዋዋይ ሀገራት ላይ ከሚያስቀምጣቸው ግዴታዎች አንዱ ከሥራ ጋር የተገናኘ የጤና እክል እና አደጋን በመከላከል በሥራ ቦታ የሚፈጠር ጉዳትን ለመቀነስ የሚያስችል ብሔራዊ ፖሊሲ ሊኖር  ይገባል። በዚህ መሠረትም ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሙያ ደኅንነትና ጤንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ አላት።

መ.ማኅበራዊ ዋስትና (Social security)፡ መሠረታዊ የሰብአዊ መብት ሲሆን ከወጣትነት ጊዜ ጀምሮ የጡረታ ዘመንን ጨምሮ በሕይወት ሊፈጠር ከሚችል ድንገተኛ ሁኔታ እና የሥራ ላይ አደጋ ጥበቃ የሚሰጥ ነው። ማኅበራዊ ዋስትና የጥሩ ሥራ አንዱ አካል ሆኖ እንዲቀጥል ከአስቻሉት መርሖች በአጋርነት፣ በሁለንተናዊነት፣ እኩልነት ላይ የተመሠረተ እንዲሁም የተሟላና አስገዳጅ ሽፋን የሚሰጥ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ዐቅም በፈቀደ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማኅበራዊ ዋስትና እንዲኖረው መደረግ እንዳለበት እና ፖሊሲዎቹም ይህን ታሳቢ እንዲያደርጉ ይደነግጋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ማኅበራዊ ዋስትና ጥበቃ ማዕቀፍን ፈርማለች፤ ብሔራዊ የማኅበራዊ ጥበቃ ፖሊሲም አላት። የማኅበራዊ ጥበቃ ብሔራዊ ፖሊሲው አደጋን፣ ተጋላጭነትን እና ድህነትን ለመቀነስ ያለመ ነው። የፖሊሲው ትኩረትም የሰዎችን ድህነት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አደጋዎችን መቀነስ ነው። ይህም ገቢን ማጠናከር፣ የሰዎችን ሕይወት ማሻሻል እና ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ማኅበረሰቦች ሕጋዊ ከለላ መስጠትን ይጨምራል።

ሠ. በቂ የኑሮ ደረጃ ለመኖር የሚያስችል ደመወዝ (Living Wage)፡ የጥሩ ሥራ አንዱ አካል ሲሆን የሠራተኛው ዝቅተኛ መሠረታዊ ፍላጎትን ማሟላት፣ ቤተሰብን መደገፍ እና በክብር ማኖር የሚያስችል ደመወዝ ማለት ነው። የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባሕል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን ላይ እንደተደነገገው ለሠራተኞች የሚከፈለው ክፍያ ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን በደህና ሁኔታና በበቂ የኑሮ ደረጃ ለማኖር የሚያስችል መሆን ይኖርበታል። ይህም ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ የማግኘት መብትን ይጨምራል።

የጥሩ ሥራ እጦት ወይም የኢኮኖሚ ሁኔታ ሰዎችን ለመጥፎ የሥራ ሁኔታ፣ ለዝቅተኛ ደመወዝ እና ምንም ዐይነት ማኅበራዊ ዋስትና ለሌለበት ሁኔታ ያጋልጣል። በእንደዚህ ዐይነት ሁኔታ መሥራት በተለይም መደበኛ ባልሆነ ሥራ ውስጥ መሠማራት በታዳጊ ሀገራት የተስፋፋ ሲሆን፤ በተለይም ሴቶች፣ ሕፃናት እና የአካል ጉዳተኞች ለእንደዚህ ዐይነት  የመብት ጥሰቶች ተጋላጭ ናቸው።

ጥሩ ሥራን ማስጠበቅ ምን ዐይነት ጠቀሜታ ይኖሩታል?

ጥሩ ሥራ ሠራተኛው በበቂ የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲኖር ያስችላል። በተጨማሪም ሥራ የገቢ ምንጭ እንደመሆኑ ቁሳዊ ፍላጎትን ለማሟላት፣ የተረጋጋ ቤተሰብን ለመምራት እና የተሻለ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ለመፍጠር ይረዳል። ሁሉንም የማኅበረሰብ አባል የሚጠቅም፣ ቀጣይነት ያለው እና አካታች የሆነ የኢኮኖሚ እድገትን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ ምርታማነትን በመጨመር የኢኮኖሚ እድገትን ያመጣል። ማኅበራዊ ትስስርን ያጠናክራል በተለይም ወጣቶች  የግጭት  ቡድኖችን ከመቀላቀልና አመጽ ውስጥ ከመግባት ይታደጋል።

ጥሩ ሥራን ተፈጻሚ ለማድረግ ምን ያስፈልጋል?

  • የሰው ኃይል ደኅንነትን የሚያስጠብቅና ከጉልበት ብዝበዛ የሚታደግ ሕግ ያስፈልጋል። የአሠሪና ሠራተኛ መብትን ለማስጠበቅ ከወጣ ሕግ ጎን ለጎን በሀገር ውስጥ ላለ የሰው ኃይል ጥበቃ ተያያዥ የጤናና ደኅንነት ሕጎችን ተፈጻሚ ማድረግ ወሳኝነት አለው። ሠራተኛውም በበቂ የኑሮ ደረጃ ለመኖር እንዲችል ዝቅተኛ የደመወዝ እርከን የሚያስቀምጥ ሕግ ማውጣት ትልቅ ጠቀሜታ አለው።
  • በሀገር ኢኮኖሚ እና በሥራ ገበያ ሁኔታ ላይ የተሟላና ወቅቱን የጠበቀ መረጃ ያስፈልጋል። ይህ መረጃ ዝቅተኛውን (ተገቢውን) የደመወዝ እርከን ለማስቀመጥ እና በየጊዜው ወቅታዊ ለማድርግ ይረዳል።
  • ጥሩ ሥራን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የትብብር ሥራ እና በቂ የፋይናንስ ድጋፍ ያለው የሠራተኛ አስተዳደር ሥርዓት አስፈላጊ ነው።
  • የጥሩ ሥራ ዕድልን ለመፍጠር ጥራት ካላው ትምህርትና ሥልጠና በተጨማሪ ገበያው የሚፈልገው ክህሎት ሊኖር ይገባል።  ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገትን የሚያስገኙ፣ እንዲሁም ምርታማ የሥራ ዕድልን የሚፈጥሩ የቴክኒክ፣ የሙያና የአመራር ስልጠና ፕሮግራሞችን፣ ዘዴዎችን እና ፖሊሲዎችን መንደፍ  እና ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።

Related posts

April 26, 2023April 26, 2023 Human Rights Concept
ጤናማ እና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት
April 12, 2023April 24, 2023 Human Rights Concept
በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት
December 29, 2022August 28, 2023 Event Update
በግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሪፖርት የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ ኮሚሽኑ ቀጣይነት ያለው የውትወታ ሥራዎች ይሠራል
September 9, 2022October 6, 2022 Human Rights Concept
የሠራተኞች ሰብአዊ መብቶች

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.