Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በኢትዮጵያ እውነትን የማወቅ መብትን ጨምሮ የሽግግር ፍትሕ ላይ እየተካሄደ ያለ አውደ ጥናት

March 24, 2022August 28, 2023 Event Update, ስብሰባዎች እና ሌሎች ዝግጅቶች

ስብሰባው የሚካሄድበት ቀን ከእ.ኤ.አ. 2010 ጀምሮ መጋቢት 15 ቀን የሚታሰበው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ እውነቱን የማወቅ መብት እና የተጎጂዎች ሰብአዊ ክብር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታሰብበት ዕለት ነው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ
መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ (East Africa Regional Office of the United Nations High Commissioner for Human Rights (OHCHR-EARO) በጋራ በመሆን ከመጋቢት 15 እስከ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን፣ ሲቪል ማኅበራትን፣ የተ.መ.ድ. ኤጀንሲዎችን፣ አህጉራዊ ድርጅቶችን (Regional Organisations)፣ ምሁራንንና አህጉራዊ ባለሙያዎችን ያሳተፈ እውነትን የማወቅ መብትን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ በሚል ርዕስ የምክክር መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡ ስብሰባው የሚካሄድበት ቀን ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ እውነቱን የማወቅ መብት እና የተጎጂዎች ሰብአዊ ክብር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታሰብበት ዕለት ሲሆን፣ ቀኑ ከእ.ኤ.አ. 2010 ጀምሮ በየዓመቱ መጋቢት 15 (ማርች 24 ) ይታሰባል።

ስብሰባው ኢሰመኮ እና OHCHR-EARO በትግራይ ክልል ላይ ባካሄዱት የጣምራ ምርመራ ሪፖርት ውስጥ የተዘረዘሩ ምክረ ሃሳቦች ውጤታማ፣ የተቀናጀ እና ጊዜውን የጠበቀ ትግበራ እንዲኖራቸው፤ በተለይም ከሽግግር ፍትሕ ጋር ተያያዥ የሆኑ ምክረ ሃሳቦችን ለማገዝ ከሚሰሯቸው ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡ በጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው የጣምራ ሪፖርት ለተለያዩ አካላት ተለይተው የተዘጋጁ 59 ምክረ ሃሳቦችን በግጭቱ ተሳታፊ ለሆኑ ወገኖች፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ እና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ያቀረበ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል አንዱ የሰብአዊ መብቶችን መርሆች የሚያሟላ ፣ ሁሉን አቀፍ እና ተጎጂዎቸን ማዕከል ያደረገ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓት (transitional justice mechanism) እንዲቋቋም የሚለው ይገኝበታል።

የአውደ ጥናቱ ዋና ዓላማ ባለድርሻ አካላት እውነትን የማወቅ መብትን ጨምሮ የሽግግር ፍትሕ አካል የሆኑ ጽንሰ ሃሳቦች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለመጨመር ሲሆን፣ በስብሰባው ሌሎች ሀገራት በሽግግር ፍትሕ ያላቸው ተሞክሮዎች የሚጋሩ ይሆናል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ እና ማዕቀፍ ሊዘጋጅ ስለሚችልበት ሁኔታና ሌሎች ጉዳዮች ውይይት ይደረጋል። 

እውነትን የማወቅ መብት ጋር ተያይዞ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በመክፈቻ ንግግራቸው “ጣምራ ምርመራው በተደረገበት ወቅት ተጎጂዎች በእራሳቸውና በቤተሰብ አባሎቻቸው ላይ ስለደረሰው ጉዳት እውነቱን ማወቅ እንደሚፈልጉ እና በግጭቱ የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች ተጎጂዎች የደረሰባቸውን የመብቶች ጥሰት እና በደል እውቅና ሰጥተው ኃላፊነት እንዲወስዱ እንደሚፈልጉ ለምርመራ ቡድኑ ገልጸዋል” ብለዋል። በተጨማሪም ዋና ኮሚሽነሩ ከሁሉም የሰብአዊ መበቶች በደል እና ጥሰት የደረሰባቸው ተጎጂዎች ጎን የሚቆሙ መሆናቸውን ገልጸው፣ ኢሰመኮ እውነትን የማጋለጥና ጥሰቶችን የመሰነድና ሪፖርት የማድረግ ሥራውን፣ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች በደል እና ጥሰት ለሚደርስባቸው ሰዎች ፍትሕ እንዲረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል። 

የOHCHR-EARO ተወካይ ማርሴል ክሌመንት አክፖቮ በበኩላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች፣ወንዶች እና ሕፃናት በግጭቱ ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት የደረሰባቸውንና እየደደረሰባቸው ያሉ ሰዎችን ሁኔታና በግጭት ውስጥም ቢሆን የመቻቻልን፣ የዕርቅን እና የውይይትን መልዕክቶች ለማስተላለፍ ጸንተው ለቆሙ እውቅና ሰጥተዋል፡፡ አክለውም የተለያዩ ሀገራት የራሳቸው የሆነ የፍትሕ ራዕይ ያላቸው በመሆኑ የተጎጂዎችን ፍላጎት በሚያጣጥም መልኩ የኢትዮጵያ ባሕላዊ (ቅርሳዊ)፣ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ አውድ ሊታሰብ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የቪድዮ መልዕክት ያስተላለፉት በተ.መ.ድ. የእውነት፣ የፍትሕ፣ የመልሶ መቋቋምና ጥሰቶች እንዳይደገሙ ዋስትና የማግኘት ጉዳዮች ልዩ ዘጋቢ የሆኑት ፋቢያን ሳልቪኦሊ፣ የሽግግር ፍትሕ ሂደት ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ፣ የሥርዓተ-ጾታ አመለካከቶችን የሚያካትትና ዓለም አቅፍ የሰብአዊ መብቶች መስፈርቶችን የሚያከብር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ልዩ ዘጋቢው የሽግግር ፍትሕ ሂደት አምስቱ ምሰሶዎች እውነትን የማወቅ መብት፣ ፍትሕ የማግኘት መብት፣ መልሶ መቋቋም፣ ጥሰቶች እንዳይደገሙ የሚወሰዱ የዋስትና እርምጃዎች እንዲሁም የመታሰብያ/ የማስታወሻ ሥራዎች (memorialization) መሆናቸውን አብራርተው፣ እነዚህ አምስት ምሰሶዎች እርስ በራሳቸው መደጋገፍ እንደሚኖርባቸው አጽኖት ሰጥተዋል። በመጨረሻም ልዩ ዘጋቢው በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲጀመር ለማስቻል ቴክኒካል (ሙያዊ) እገዛ ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡

የውይይት መድረኩ ኢትዮጵያ እንደ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ያሉ ሰላምን ለመመለስ የሚያግዙ መልካም እርምጃዎች እየወሰደች በምትገኝበት ወቅት የሽግግር ፍትሕ መዋቅር ሊኖር የሚችልበትን እድል በተመለከተ ከሚደረጉ ተከታታይ ዝግጅቶች መካከል የመጀመሪያው ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ኢሰመኮ የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን በጠበቀ መልኩ አካታች የሆነ የእርቅ ሂደት እንዲኖር ሙሉ ድጋፍ አንዲያደርጉ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሪ ያቀርባል፡፡

ለእንግሊዘኛው ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንን ይጫኑ

Related posts

December 10, 2021August 26, 2023 EHRC Quote
ኢሰመድህ ከተ.መድ. የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የምስራቅ አፍሪካ ጽ/ቤት (UNOHCHR - EARO) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መርኃ ግብር ለኢሰመኮ ምስጋና አቀረበ
November 30, 2021October 3, 2023 1st Film Festival
ኢሰመኮ እና ኢሰመድህ በኅዳር እና በታኅሣሥ ወራት 2014 ዓ.ም. ታስበው የሚውሉ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀናትን በተለያዩ ዝግጅቶች ያከብራሉ
December 15, 2021December 15, 2021 EHRC Quote
የሚዲያ አባላት መታሰር
June 20, 2023August 28, 2023 Event Update
ሰብአዊ መብቶችን ያገናዘበ የሽግግር ፍትሕ ለማስፈን የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ሚና

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.