The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) launched on November 20, 2021 a new social media hashtag called #KeepWordSafe (#ጤናማቃላት in Amharic). Designed to promote human rights sensitive content and discourse particularly on social media, the #KeepWordSafe hashtag means keeping oneself and others from “unhealthy” words. #KeepWordSafe encourages healthy discourses by ensuring that exchanges between individuals, communities and institutions focus on ideas and not on identities.
#KeepWordSafe was officially designed at a training in Bishoftu held from November 17 to November 18, 2021. Youth participants with an active social media engagement who are university students, recent graduates and representing various associations took part in the training on basic human rights concepts and skills. The participants will officially introduce #KeepWordSafe on the occasion of #WorldChildren’sDay marked each year on November 20.
The introduction of #KeepWordSafe will be followed by similar social media campaigns on upcoming international days until the end of 2021 including Prevention of Violence Against Women Day (November 25), Persons with Disability Day (December 3), Volunteer for Socio-Economic Day (December 5), Anti-Corruption Day (December 9), Human Rights Day (December 10), Universal Health Coverage Day (December 12), Migrants Day (December 18) and Day of Solidarity (December 20). The Commission will provide the necessary technical support to participants as they generate their own content to promote #KeepWordSafe and the international days.
Join the #KeepWordSafe movement too to contribute to human rights sensitive discourse and content on social media and other platforms.
Keep your words safe, keep yourself from unsafe words, promote #KeepWordSafe.
Introducing #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኅዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጥቅም ላይ የሚውል #ጤናማቃላት (በእንግሊዘኛ መጠርያው #KeepWordSafe) የተሰኘ የማኅበራዊ ሚድያ “ሃሽታግ” ይፋ አደረገ። #ጤናማቃላት በተለይም በማኅበራዊ ሚድያ የሚደረጉ ውይይቶች ይዘት ሰብአዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ እንዲደረጉ ፍላጎት ያለው ማንኛውም ግለሰብ ሊጠቀመው እንዲችል የታለመ ነው። #ጤናማቃላት በግለሰቦች፣ በማኅበረሰቦች እና በተቋማት መካከል የሚደረጉ ውይይቶች ጥላቻ እና ግጭት እንዳያነሳሱ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ፣ ክርክሮች በሃሳብ ላይ እንጂ በማንነት ላይ ያተኮሩ እንዳይሆኑ ይረዳሉ።
#ጤናማቃላት የሚለው ሃሽታግ ከኅዳር 8 እስከ ኅዳር 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚድያዎች ከፍተኛ ተሳትፎ ላላቸው ተማሪዎች፣ ምሩቆች፣ የወጣትና ሌሎች ማኅበራት ተወካዮች መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ እና ክህሎት እንዲኖራቸው በማሰብ በተሰጠ ሥልጠና በይፋ ተመርቋል። በዚሁም መሰረት ሰልጣኞቹ በተለይም ከእ.ኤ.አ. ከኅዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሚታሰቡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ቀናት አማካኝነት #ጤናማቃላት የሚለውን ሃሽታግ ለሕዝብ ያስተዋውቃሉ።
ለዚሁ የተመረጡት ቀናትም ዘጠኝ ሲሆኑ እነርሱም፡- የሕፃናት ቀን (ኖቬምበር 20 (እ.ኤ.አ.))፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የማስወገድ ቀን (ኖቬምበር 25)፤ የአካል ጉዳተኞች ቀን (ዲሴምበር 3) ፤ ለኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት የበጎ ፈቃደኞች ቀን (ዲሴምበር 5)፤ የፀረ-ሙስና ቀን (ዲሴምበር 9)፤ የሰብአዊ መብቶች ቀን (ዲሴምበር 10)፤ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ቀን (ዲሴምበር 12) የፍልሰተኞች ቀን (ዲሴምበር 18) እና የወንድማማችነትና እህትማማችነት ቀን (ዲሴምበር 20) ናቸው፡፡ በእነዚህ የሰብአዊ መብቶች ቀናት ዙሪያ በራሳቸው ተነሳሽነት ማኅበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው ሰብአዊ መብቶችን እና #ጤናማቃላት የሚለውን ሃሽታግ የማስተዋወቅ ዘመቻ በሚያከናውኑበት ወቅት ኢሰመኮ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል።
እርሶም #ጤናማቃላት ወይም #KeepWordSafe የሚለውን ሃሽታግ በመጠቀም ማኅበራዊ ሚድያውና ሌሎች የውይይት መድረኮች ይዘቶች ሰብአዊ መብቶችን ያከበሩ እንዲሆኑ አስተዋጽዖ ያድርጉ። #ጤናማቃላት እንጠቀም፣ #ጤናማቃላት እናበረታታ፣ #ጤናማቃላት ካልሆኑ ይዘቶች እንጠበቅ።