አድሎአዊ የዘር ልዩነቶችን ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት፣ አንቀጽ 2(1)

ይህን ስምምነት የተቀበሉ ሀገራት የዘር ልዩነትን በማውገዝ በማንኛውም መልኩ የሚገለጽ የዘር ልዩነትን ለማስወገድ የሚያስችል ፖሊሲ በተቻለ መጠንና በአስቸኳይ በመንደፍ በሰው ልጅ ዘሮች መካከል መቻቻልን ለማስፈን፦ 

  • እያንዳንዱ አባል ሀገር በሰዎች፣ በሰዎች ስብስብ ወይም ተቋሞች መካከል የዘር ልዩነት የሚፈጥር እርምጃ አይወስድም ወይም ተግባር አያካሄድም፡፡ 
  • እያንዳንዱ አባል ሀገር በሰዎች፣ በቡድኖች ወይም በተቋሞች የሚካሄድ የዘር ልዩነት ማንኛውንም ዓይነት መንገድ ተጠቅሞ መከልከልና ማስቆም አለበት። 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 25

  • በዘር፣ በብሔር፣ ብሔረሰብ፣ በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኀበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው።