ይህ መብት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰንሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫዘዴ ማንኛውንም አይነት መረጃ እና ሃሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነትን ያካትታል፡፡ (ዓለም አቀፍየሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ኮንቬንሽን ፤ አንቀጽ 19)

የፕሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን፤ እንዲሁም የሥነ ጥበብፈጠራ ሥራ ነፃነት መከበር ሃሳብን በነፃነት የመግለጽመብትን እውን ለማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

የፕሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን፤ እንዲሁም የሥነ ጥበብሥራ ፈጠራ ነጻነት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥቱ ተረጋግጧል፡፡ የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃየማግኘት ዕድል እና የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩየተከለከለ መሆኑ የፕሬስ ነፃነት በተለየ ሁኔታየሚያጠቃልላቸው መብቶች ናቸው፡፡ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገመንግሥት፤ አንቀጽ 29)