Skip to content
Facebook Twitter
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social and Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants Rights
        • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
        • Women’s and Children’s Rights
        • HR Monitoring and Investigation
        • Human Rights Education
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ሰብ አዊ ክብር፣ ነጻነት እና ፍትሕ ለሁሉም:- የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ዓመታዊ ፊልም ፌስቲቫል ሁለተኛ ዙር በአዳማ፣ በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በሃዋሳ እና በጅግጅጋ ይካሄዳል

December 10, 2022December 14, 2022 Press Release

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ እና የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ ለማዳበር ሰፊ ተደራሽነት ያለውን የፊልም ጥበብን በመጠቀም በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ፊልሞች ለእይታ እና ለውይይት ይቀርባሉ

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ የተጀመረው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ለመጀመሪያ ጊዜ ከኅዳር 28 እስከ ታኅሣሥ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዳማ፣ በአዲስ አበባ እና በሃዋሳ ከተሞች መካሄዱ ይታወሳል። ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ አዲስ አበባን ጨምሮ በአምስት ከተሞች የሚካሄደው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ታኅሣሥ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ጀምሯል።

ሰብአዊ ክብር፣ ነጻነት እና ፍትሕ ለሁሉም በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ሰፊ ተደራሽነት ያለውን የፊልም ጥበብን በመጠቀም እና ስለ ሰብአዊ መብቶች ያለውን ግንዛቤ ለማዳበር በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ፊልሞች በፌስቲቫሉ ለእይታ እና ለውይይት ይቀርባሉ። በፌስቲቫሉ ሰብአዊ መብቶችን ማዕከል ያደረጉ አዳዲስ እና ከዚህ በፊት ለዕይታ የቀረቡ በዓለም አቀፍ መድረኮች ጭምር ተቀባይነትን ያተረፉ የሙሉ ጊዜ እና አጫጭር ፊልሞች እንዲሁም ዘጋቢ ፊልሞች ለዕይታ ይቀርባሉ፡፡

በአምስቱ ከተሞች የሚካሄደው ሁለተኛው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል፡-

  • በአዳማ- ታኅሣሥ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. በኦሊያድ ሲኒማ፣ 
  • በአዲስ አበባ- ታኅሣሥ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቴአትር እና ባህል አዳራሽ 
  • በባሕር ዳር- ታኅሣሥ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በሙሉ ዓለም የባህል ማዕከል፣ 
  • በሃዋሳ- ታኅሣሥ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ሌዊ ሲኒማ እንዲሁም፣
  • በጅግጅጋ- ታኅሣሥ 9 ቀን 2015 ዓ.ም. በኤምሲኤም ሆቴል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

15 ፊልሞች ለእይታ የተሰናዱበትና በመዓዛ ወርቁ ፊልም ፕሮዳክሽንስ አስተባባሪነት የሚዘጋጀው ይህ ፌስቲቫል በሴቶችና ሕፃናት መብቶች፣ በስደተኞች፣ ፍልሰተኞች እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች፤ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች፣ በፍትሐዊ እና ሰብአዊ የሥራ ክፍፍል፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ እና ጥቃት፣ እንዲሁም በማረሚያ ቤት የወጣት ጥፋተኞች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ የሚያጠነጥኑ ፊልሞች ተካተውበታል፡፡ ፊልሞቹ በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ሲዳምኛ ቋንቋዎች የተሠሩ ወይም አጋዥ ጽሑፍ (subtitle) አካተዋል፡፡

ፌስቲቫሉን በይፋ ለማስጀመር በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ በሀገራችን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አሁን ላለበት አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ለመድረሱ ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም፤ ስለ ሰብአዊ መብቶች ያለው አነስተኛ ግንዛቤ በአሉታዊ መልኩ አስተዋዖ አድርጓል ብለዋል። አክለውም ኢሰመኮ በአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱ ከለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮች መካከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት እንዲኖር ማስቻል ሲሆን የኪነጥበብ ዘርፉ የሰብአዊ መብቶችን ግንዛቤ ከማስፋፋት እና ከማስተማር አኳያ ከፍያለ ሚና ይጫወታል። ይህ የሰብአዊ መብቶች ዓመታዊ የፊልም ፌስቲቫል በሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ለመወያየት፣ ለመመማማር እና በሰብአዊ መብቶ መርሆች የታነጸ ትውልድን ለመቅረጽ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል። 

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በበኩላቸው ኢሰመኮ “ሰብአዊ መብቶች ባሕል የሆኑባት ኢትዮጵያን ማየት” የሚለውን ራዕይ ለማሳካት የትምህርትና የስልጠና ተቋማት፣ ማኅበራዊ ሚዲያን ጨምሮ መገናኛ ብዙኃንና የኪነጥበብ ዘርፉ የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤን ለማዳበር፣ የሰብአዊ መብቶች ሥራዎችን ለማስተዋወቅ እና ለማኅበረሰቡ ለማሰራጨት አስተዋጽዖ ያላቸው በመሆናቸው ትኩረት የሚሰጣቸው ናቸው ብለዋል።

በፌስቲቫሉ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው በፊልም እና በሌሎች የኪነጥበብ ዘርፍ ሙያ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች፣ በሰብአዊ መብቶች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የሚሠሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኀን፣ ተማሪዎች እና ሌሎች ተመልካቾች ይታደሙበታል፡፡

በፌስቲቫሉ የሚቀርቡ ፊልሞች ዝርዝር እዚህ ተያይዟል

Location Addis Ababa

Reports & Press Releases

December 4, 2021December 4, 2021 EHRC on the News
Ethiopia’s human rights watchdog is still criticizing all parties to the escalating conflict – The Danish Institute for Human Rights
November 28, 2021January 4, 2022 EHRC on the News
Online-Discussion: Human rights, transitional justice and the difficult search for a political solution in Ethiopia – German Africa Foundation (DAS)
December 3, 2022December 3, 2022 Event Update
EHRC Disability Rights and Rights of Older Persons Commissioner Rigbe Gebrehawaria's message on #IDPD2022
December 10, 2021February 20, 2022 EHRC Quote
ኢሰመድህ ከተ.መድ. የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የምስራቅ አፍሪካ ጽ/ቤት (UNOHCHR - EARO) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መርኃ ግብር ለኢሰመኮ ምስጋና አቀረበ

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social and Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants Rights
    • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
    • Women’s and Children’s Rights
    • HR Monitoring and Investigation
    • Human Rights Education
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.