የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 12(2) እና አንቀጽ 18 (2)(ለ) 

  • አባል ሀገራት፦ 
    • በሴቶች ዘንድ ማንበብ እና መጻፍን ለማስፋፋት፣ 
    • በሁሉም ደረጃዎችና በሁሉም የትምህርት ዘርፎች በተለይም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለሴቶች የሚሰጡ ትምህርትና ስልጠናዎችን ለማስፋፋት ዝርዝር አወንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው።
  • አባል ሀገራት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ በአዲስና ታዳሽ የኃይል ምንጮች እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎች ላይ ምርምርንና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት፣ በዚሁም ላይ የሴቶችን ተደራሽነት እና የቁጥጥር ተሳትፎ ለማመቻቸት ተገቢውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ ይገባቸዋል።