Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ እና መዝሙር ውዝግብና ተያያዥ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችን በተመለከተ

December 28, 2022August 28, 2023 Public Statement

ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ወደፊትም እንዳያጋጥሙ ለችግሩ መንስኤ ለሆነው የሰንደቅ ዓላማ እና መዝሙር ውዝግብ ሕፃናትን ጨምሮ ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ ግልጽ የሆነ የሕግ እና ፖሊሲ መፍትሔ በማበጀት ዘላቂ እልባት መስጠት ይኖርባቸዋል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በአፋን ኦሮሞ ትምህርት በሚሰጥባቸው የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማን መስቀልና የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እንዲዘመር ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ውሳኔውን በሚቃወሙ እና በሚደግፉ ተማሪዎች መካከል በተከሰተው ውዝግብና ግጭት ምክንያት የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ያስከተለውን የሰብአዊ መብቶች እንድምታ በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ 

ምንም እንኳን የጸጥታው ሁኔታ በአሁኑ ወቅት በተወሰነ ደረጃ ጋብ ያለ ቢሆንም፤ ለወደፊቱም ይህን መሰል ሁኔታዎችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በዘላቂነት ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፤ ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትልና ምርመራ የተረጋገጡ ግኝቶችን፣ ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ማዕቀፎች አንጻር በመተንተን ጭምር ይህን ምክረ ሃሳብ ለማቅረብ ይወዳል፡፡ 

ኮሚሽኑ ባደረገው ምርመራና ክትትል የጸጥታ መደፍረስ የተከሰተባቸውን ሁሉንም ትምህርት ቤቶች የሚሸፍን ምርመራ ለማካሄድ ባይቻልም፤ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን፣ መምህራን እና ኃላፊዎችን፣ በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች በእስር ላይ የነበሩ ተማሪዎችንና ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም በማነጋገር፣ የጸጥታ ችግር ተከስቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች የነበሩ ምስክሮችንና የተማሪዎች ወላጆችን እንዲሁም የፖሊስ አባላትን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሌሎች ኃላፊዎችን በማነጋገርና መረጃዎችና ማስረጃዎች በማሰባሰብ ስለ ጠቅላላ ጉዳዩ ተገቢውን ግንዛቤ ለማግኘት ተችሏል፡፡

  1. ዋና ዋና ግኝቶችና የሰብአዊ መብቶች እንድምታዎች 
  • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ በአፋን ኦሮሞ ትምህርት በሚሰጥባቸው የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለተከሰተው የጸጥታ መደፍረስ መነሻው በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማን መስቀልና የክልሉ መዝሙር እንዲዘመር ማድረግን በሚመለከት የተለያየ ሃሳብና ፍላጎት ባላቸው ተማሪዎችን ጨምሮ የትምህርት ቤቶቹ ማኅበረሰብ አባላት መካከል የተፈጠረ አለመግባባትና ግጭት ነው፡፡ 
  • የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በአፋን ኦሮሞ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ የመስቀልና የክልሉን መዝሙር የመዘመር መብት አላቸው በሚል መነሻ በትምህርት ቤቶቹ ግቢ ውስጥ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ ከፌዴራሉ መንግሥት ሰንደቅ ዓላማ ጎን በመስቀልና ጠቅላላው ተማሪዎች የክልሉን መዝሙር በመዘመር የሰንደቅ ዓላማ ሥርዓቱን እንዲያከብሩ በመደረጉ በየትምህርት ቤቶቹ በሚገኙ ከፊል የትምህርት ቤቶቹ ማኅበረሰብ አባሎች እርምጃው ሕጋዊ መሠረት የለውም በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ 
  • በአብዛኛው ቦታዎች የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ መሰቀልና የክልሉ መዝሙር መዘመርን በሚደግፉና በሚቃወሙ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ሁከት፣ ረብሻና ግጭት፤ እንዲሁም የፖሊስ አባላት ሁኔታውን ለመቆጣጠር በወሰዱት የእስር እርምጃ የሰብአዊ መብቶች አሉታዊ እንድምታ ያስከተለ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ 
  • የትምህርት ሂደት በመስተጓጎሉ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ከባድና ቀላል የአካል እና የሥነ ልቦና ጉዳት ደርሷል፣ የተማሪዎችና የትምህርት ቤቶች ንብረት ወድሟል፣ ሕፃናት ተማሪዎች ለአካላዊ እንግልት እና ከሕግ ውጭ ተገቢ ላልሆነ እስር ተዳርገዋል፡፡ 
  • ይሁንና በማኅበራዊ ሚዲያ እና በአንዳንድ ተቋሞችም የተዘገበውና ጉራራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ውስጥ የነበረ ተማሪ ሕይወት ጠፍቷል የተባለው ትክክለኛ መረጃ አለመሆኑንና በዚህ ክስተት የደረሰ የሕይወት መጥፋት አለመኖሩን ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡ 
  • በንብረት ላይ የደረሰው ውድመትና በረብሻው ወቅት በተማሪዎች ላይ የደረሰው ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት በተማሪዎቹ የእርስ በእርስ ግጭት የተከሰተ ሲሆን፤ በአካባቢው የነበሩ በርካታ ምስክሮች ለኮሚሽኑ እንዳስረዱት ፖሊስ ብዙ ተማሪዎችን ከማሰሩ በስተቀር፤ አብዛኛዎቹ የፖሊስ አባላት በጥንቃቄና ተመጣጣኝ በሆነ እርምጃ ሁከቱን ለማረጋጋት ይጥሩ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
  • እንዲሁም ፖሊስ አብዛኛዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ተጠርጣሪ ተማሪዎች በፍጥነት ወደ የሕፃናት ልጆች ችሎት እና መደበኛ ፍርድ ቤት እያቀረበ ከፍርድ ቤት በተሰጠ የዋስትና መብት በተለያየ ጊዜ ከእስር ተለቀዋል፡፡ በተለይም ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን ፖሊስ በፍጥነት ወደ ሕፃናት ችሎቶች እንዲቀርቡ እያደረገ ወዲያውኑ ተለቀዋል፡፡ 
  • በአንጻሩ እጅግ ብዙ ዕድሜያቸው በአብዛኛው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ተማሪዎች ከመነሻውም ቢሆን ለእስር መዳረጋቸው እና ለተለያየ ጊዜ መጠን በእስር መቆየታቸው ተገቢ ያልሆነና ለነገሩ ሁኔታም ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ነው፡፡ 
  • የጸጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ በሆነ እርምጃ ሁከቱን በመቆጣጠር፣ እጅግ ቢበዛ ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ ተማሪዎቹን በየትምህርት ቤታቸው ግቢ ወይም ባሉበት ቦታ እንዲቆዩ አድርገው፣ በቀጥታ በወንጀል ተግባር ላይ የነበሩ ተማሪዎች ካሉም እንደአስፈላጊነቱ እጅግ አጭር ለሆነ ጊዜ ብቻ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ቆይተው ሳይውል ሳያድርና እንደአግባብነቱ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 28(1) መሰረት በፖሊስ ጣቢያ በሚሰጥ ዋስትና መልቀቅ ሲገባቸው፤ ከዚህ ውጪ ብዙ ሕፃናት ተማሪዎችን የተሟላ አገልግሎት በሌላቸውና ለአካለ መጠን የደረሱ ተጠርጣሪዎች በሚታሰሩባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች አስረው ማቆየታቸው የአስፈላጊነት፣ የሕጋዊነትና የተመጣጣኝነት መርሆችን ያልተከተለ የሕፃናትን መብቶች የሚጥስ ተግባር ነው፡፡ 
  • በተማሪዎች ተፈጽሟል የሚባል ጥፋት ቢኖርም እንኳን ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን በሚመለከተው የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችና አግባብነት በአላቸው የኢትዮጵያ ሕጎች መሠረት ለሕፃናት ልጆች የሚገባው የሕግ ከለላ እንደተጠበቀ ሆኖ የማጣራት ሥራ ከማከናወን በስተቀር፤ ሕፃናት ተማሪዎችን ሊያውም በጅምላ ለእስር መዳረግ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እርምጃ በመሆኑ ለወደፊቱ ሊደገም የማይገባ ነው፡፡

2. የሰንደቅ ዓላማውና የብሔራዊ መዝሙር ውዝግብና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው

  • ለዚህ ሁከትና ለደረሰው የሰብአዊ መብቶች ጉዳት መነሻ ምክንያት የሆነውን የሰንደቅ ዓላማ እና የብሔራዊ መዝሙር አጠቃቀም ሕጋዊ መሠረት እና ምክንያት መፈተሽም ለወደፊቱ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን ለመከላከል አስፈላጊ ነው፡፡ 
  • በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49 እንደተደነገገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ያለው፣ ተጠሪነቱ ለፌዴራሉ መንግሥት የሆነ እና የከተማው ነዋሪዎችም በፌዴራሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወከሉ ሲሆኑ፤ የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም የሚጠበቅለት መሆኑና ዝርዝሩ በሕግ እንደሚወሰን የተገለጸ ቢሆንም እስከአሁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዝርዝር ሕጉን ያላወጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡ 
  • በኢትዮጵያ መንግሥት የግዛት ወሰን ውስጥ እና የክልልና የከተማ መስተዳድሮችን ጨምሮ በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች፣ ንግድ መርከቦችና አውሮፕላኖች ላይ ተፈጻሚ በሚሆነው የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ሰንደቅ ዓላማ በየቀኑ ወይም ቢያንስ በብሔራዊ በዓል ቀን የሚሰቀልባቸው ቦታዎችና የሰንደቅ ዓላማ አሰቃቀልና አጠቃቀም ሥነ ሥርዓት በዝርዝር ተደንግጓል፡፡  
  • በፌዴራል ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 3 (3) መሠረት ክልሎች የየራሳቸው ሰንደቅ ዓላማና አርማ ሊኖራቸው እንደሚችል በደነገገው መሠረትና በየክልሎቹ በጸደቁ የክልል ሕገ መንግሥትና የክልል ሰንደቅ ዓላማ አዋጆች መሠረትም የየክልሉ የሰንደቅ ዓላማ አሰቃቀልና አጠቃቀም ሥነ ሥርዓት የሚደነግጉ ሲሆን ሁሉም የክልል ሰንደቅ ዓላማ አዋጆች በየክልሉ ከፌዴራሉ መንግሥት ሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ጋር በአንድነት ተፈጻሚ የሚሆኑ ናቸው ፡፡ 
  • ከዚህ ውጪ የአንድ ክልል ሰንደቅ ዓላማ በሌላ ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ወይም የግል ተቋሞች ውስጥ እንዲሰቀል የሚያስችል የሕግ መሠረት የለም፡፡ 
  • በአንጻሩ በየትኛውም ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር የአንድ የሌላ ክልል መለያ በሆነ ተቋም ሕንጻ ላይ ወይም ግቢ ውስጥ (ለምሳሌ በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሕንጻዎች ላይ) በክልሉ ወይም በከተማው መስተዳድር ዕውቅና የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ከፌዴራሉ ሰንደቅ ዓላማ ጋር በአዋጅ ቁጥር 654/2001 በተመለከተው መሠረት መስቀል የሚከለክል የሕግ ምክንያትም የለም፡፡ 
  • ከዚህ በላይ ከተገለጹት ሕጋዊና ምክንያታዊ የሰንደቅ ዓላማ አጠቃቀም ውጪ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ውስጥ የሚገኙ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ወይም የሕዝብ አገልግሎት ተቋሞች የሌላ ክልል ሰንደቅ ዓላማን በአስገዳጅነት ለመስቀል መጣር ሕጋዊ መሠረት የሌለው ከመሆኑም በላይ አላስፈላጊ ውዝግብና ሁከት በመፍጠር ለሰብአዊ መብቶች መጣስ ሥጋት የሚፈጥር ድርጊት በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ 
  • በሰንደቅ ዓላማ ሥነ ሥርዓት ወቅት የሚዘመረውን ብሔራዊ መዝሙር በተመለከተ በፌዴራል ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 4 በግልፅ እንደተመለከተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር አንድ ብሔራዊ መዝሙር ሲሆን፤ በአዋጅ ቁጥር 673/2002 አንቀጽ 5 እንደተመለከተው ክልሎች በሕግ በወሰኑት የሥራ ቋንቋ የብሔራዊ መዝሙሩ የግጥም ይዘትና ዜማ እንደተጠበቀ ሆኖ በክልሉ የሥራ ቋንቋ በማስተርጎምና በየክልሎቹ ምክር ቤቶች በማስፀደቅ ብሔራዊ መዝሙሩ እንዲዘመር ማድረግ አለባቸው፡፡ 
  • ከዚህ ሕጋዊና ምክንያታዊ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር አጠቃቀም ውጪ አላስፈላጊ ውዝግብና ሁከት መፍጠር ለሰብአዊ መብቶች መጣስ ሥጋት የሚፈጥር ድርጊት በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ 
  • በተጨማሪም መንግሥት በሰብአዊ መብቶች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ውሳኔዎች፣ ደንቦች፣ ፕሮግራሞች፣ መርኃ ግብሮች ወይም አሠራሮች ሲዘጋጁ ወይም ከመተግበራቸው በፊት በሰብአዊ መብቶች ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን አሉታዊ ውጤቶች አስቀድሞ መለየት፣ ማጤንና መከላከል ወይም መቀነስ የሚቻልበትን መንገድ ተግባራዊ ሊያደርግ ይገባል። ይህም የመንግሥት ደንቦች፣ ፕሮግራሞች፣ መርኃ ግብር ወይም አሠራሮች መንግሥት ሰብአዊ መብቶችን ከማክበር፣ ከማስከበር እና ከማሟላት አኳያ ካሉት ግዴታዎች ጋር እንዳይቃረን  ለማድረግ ያስችላል።

3. ስለ ሕፃናት ተማሪዎች ልዩ ጥበቃ 

በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችና በኢትዮጵያም ሕጎች መሠረት የሕፃናት ልዩ ልዩ መብቶች የተጠበቁ ሲሆን፤ በተለይ የሕፃናት ልጆች በትምህርት ቤትና አካባቢ የሚደረግ ልዩ ትኩረትና ጥበቃን በሚመለከትም ዓለም አቀፍ ግዴታዎችና መርሆች አሉ፡፡

ከእነዚህም ውስጥ፡- 

  • በትምህርት ቤቶች ውስጥ አመጽ፣ ማስፈራራትና የኃይል እርምጃ የሕፃናት ልጆችን በምቹ ሁኔታ የመማርና የማደግ መብት የሚጎዳ፣ ለሥነ ልቦና ጉዳት የሚያጋልጥ እና አጠቃላይ የሆነ ፍርሀት፣ ሥጋትና ጭንቀት በማሳደር ትምህርትን፣ ዕውቀትንና ዕድገትን የሚጎዳ በመሆኑ ይህን መሰል ሥጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን በሙሉ ማስወገድ አስፈላጊ ነው፣  
  • በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሕፃናት ልጆች የሰው ልጆች ክቡርነትና እኩልነትን፣ የሃሳብ ልዩነትና መቻቻልን እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች ሙሉ እሴቶችን በሰላማዊ መንገድ የሚማሩበት የሚለማመዱበት እና የሚያጎለብቱበት ስፍራ ስለሆነ፤ ሕፃናት ልጆችን እና ተማሪዎችን በሚመለከታቸው ጉዳይ በማማከር፣ በማሳተፍና በማድመጥ የትምህርት ቤታቸው ሕይወት ውስጥ ፈቃደኛ ተሳታፊዎች ማድረግ እንጂ በኃይል፣ በዛቻ፣ በማስፈራራት፣ በማስጨነቅና በሥጋት ማስተማርና ማስተዳደር ተገቢ አይሆንም፡፡  
  • ልጆች በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ፣ ሃሳባቸውን እና ተቃውሟቸውን የመግለጽ ነጻነት ያላቸው እንደመሆኑ መጠን አስፈላጊ ክህሎቶችን የሚያጎለብቱበትን መብታቸውን በአግባቡ የሚጠቀሙበትን ምቹ ሁኔታ እና ድጋፍ በትምህርት ቤቶች ውስጥም ማመቻቸት ተገቢ ነው። 

ስለሆነም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን:- 

ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ወደፊትም እንዳያጋጥሙ ለችግሩ መንስኤ ለሆነው የሰንደቅ ዓላማ እና መዝሙር ውዝግብ ሕፃናትን ጨምሮ ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ ግልጽ የሆነ የሕግ እና ፖሊሲ መፍትሔ በማበጀት ዘላቂ እልባት በመስጠት፣ እንዲሁም አሁን በሥራ ላይ ያሉትን ሕጎች እና የሰብአዊ መብቶች መርሆችን በማክበርና በማስከበር የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በጋራ እንዲከላከሉ፤ በተጨማሪም የየትምህርት ቤቶቹና አጠቃላይ ማኅበረሰቡ በሰላም፣ በመቻቻል እና የሃሳብ ልዩነትን በመቀበልና በሰላማዊ መንገድ ብቻ በመፍታት ላይ ተመሥርቶ የመፍትሔ አካል እንዲሆን አበክሮ ያሳስባል፡፡

Related posts

March 25, 2023March 25, 2023 Event Update
አካታች፣ ተደራሽ እና ተቀባይነት ያለው የመማር ዕድል ለሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሕፃናት
September 3, 2021August 28, 2023 Press Release
የሰብአዊ መብቶች ትምህርት በመደበኛ ትምህርት ሥርአተ-ትምህርት ውስጥ በአግባቡ ሊካተት ይገባል
February 3, 2023February 6, 2023 Press Release
የሰብአዊ መብቶች ትምህርትን በመደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ የትምህርት ሥርዓቶች ውስጥ በአግባቡ ለማካተት እና ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴርና በኢሰመኮ መካከል ተፈረመ
May 27, 2023October 10, 2023 Press Release
ኢሰመኮ የሚያዘጋጀው 3ኛው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ-ችሎት (Human Rights Moot Court) ፍጻሜ ውድድር

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.