በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍን አስመልክቶ የተደረገ የአፍሪካ ኅብረት ስምምነት (የካምፓላ ስምምነት)፣ አንቀጽ 10 

  • ተዋዋይ ሀገራት በተቻለ መጠን በሕዝባዊ ወይም በግል አካላት በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ምክንያት የሚፈጠርን መፈናቀል መከላከል አለባቸው፤ 
  • ተዋዋይ ሀገራት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በፕሮጀክቶቹ ሊፈናቀሉ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ሙሉ መረጃ በመለዋወጥና ምክክር በማድረግ አዋጭ የሆኑ አማራጮችን ማጤናቸውን ያረጋግጣሉ፤ 
  • ተዋዋይ ሀገራት አንድ የቀረበ የልማት ፕሮጀክት ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ግምገማ ያካሂዳሉ፡፡