የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 20 (1) እና (2)
- ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው ከቤተሰቡ የተለየ ወይም ለራሱ ጥቅም ሲባል ከቤተሰቡ ጋር እንዲቆይ ሊደረግ የማይችል ሕፃን የመንግሥትን ልዩ ጥበቃ እና ድጋፍ የማግኘት መብት አለው።
- አባል ሀገራት በብሔራዊ ሕጎቻቸው መሠረት ከቤተሰቡ የተለየ ሕፃን አማራጭ እንክብካቤ ማግኘቱን ማረጋገጥ ይገባቸዋል።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36 (5)
- መንግሥት ለእጓለ ማውታን ልዩ ጥበቃ ያደርግላቸዋል። በጉዲፈቻ የሚያድጉበትን ሥርዓት የሚያመቻቹና የሚያስፋፉ እንዲሁም ደኅንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምዱ ተቋሞች እንዲመሠረቱ ያበረታታል።