• ብሬል በትምህርት፣ ሐሳብን የመያዝና የመግለጽ ነጻነት፣ የመረጃ ተደራሽነት እንዲሁም በማኅበራዊ አካታችነት ለዐይነ ስውራን ወሳኝ የሆነ የተግባቦት መንገድ ነው።

ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት አንቀጽ 24(3)(ሀ) እናአንቀጽ 9(2)(መ) 

አባል ሀገራት፦

  • (ዐይነ ስውራን) የሕይወትና የማኅበራዊ እድገት ክህሎት እንዲማሩ፣ ብሎም እንደ ማኅበረሰብ አባልነታቸው በትምህርት የተሟላና እኩል ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል የብሬል ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ፤
  • በሕንጻዎችና ለሕዝብ ክፍት በሆኑ ሌሎች መገልገያዎች የመረጃና የአቅጣጫ ምልክቶችን በብሬል እና በቀላሉ ለማንበብና ለመረዳት በሚያስችል ሁኔታ ለመግለጽ  ተገቢ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው፡፡