የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ 74/275፤ “ትምህርትን ከጥቃት የመጠበቅ ዓለም አቀፍ ቀን”፣ አንቀጽ 2 

የተ.መ.ድ. ጠቅላላ ጉባኤ:-

  • የሁሉም ሰዎች የትምህርት መብትን እንዲሁም በሰብአዊነት ቀውስ ሁኔታ ውስጥ ደኅንነቱ የተጠበቀና አስቻይ የትምህርት ከባቢን እና በሁሉም ደረጃዎች የትምህርት ጥራትን የማስፈን አስፈላጊነትን  በድጋሚ ያረጋግጣል። 
  • በትምህርት ቤቶች ላይ የሚሰነዘሩ ማናቸውም ጥቃቶችን እና ከዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ በሚጻረር መልኩ ትምህርት ቤቶችን ለወታደራዊ አገልግሎት ማዋልን አጥብቆ ያወግዛል፤ በሰብአዊነት ቀውስ ሁኔታ ውስጥ አስተማማኝ እና ጥበቃ የሚያስገኝ የትምህርት ቤት አካባቢን ለማስፋፋት የሚደረጉ ጥረቶችን ያበረታታል።