Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ትምህርት የማግኘት መብት

June 30, 2023August 28, 2023 Explainer

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለይ በአፍሪካ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚታሰበውን እና በየዓመቱ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 የሚውለውን የአፍሪካ ሳይንሳዊ ሕዳሴ ቀን (Africa Scientific Renaissance)፣ እንዲሁም የዓመቱ የትምህርት ወቅት መዝጊያን በማስመልከት በተዘጋጀ ማብራሪያ ትምህርት መሠረታዊ የሰብአዊ መብት መሆኑን በማስታወስ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በግጭት፣ በመፈናቀል፣ በአካል ጉዳት፣ በመሠረተ ልማት ውድመት፣ እንዲሁም በኑሮ ውድነት እና ሌሎች ምክንያቶች ከትምህርት ውጪ ሆነው ለበርካታ ወራት የቆዩ ሕፃናትን በ2016 ዓ.ም. ወደ ትምህርት እንዲመለሱ የማድረጉ ሥራ ከፍተኛ እና የተቀናጀ ትኩረት እንዲሰጠው ጥሪ ያቀርባል።

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

ማብራሪያ

ትምህርት የማግኘት መብት ምንድን ነው?

ትምህርት የማግኘት መብት ሰፊና በርካታ ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች የሚዳስስ ሲሆን ከመሠረታዊ ሰብአዊ መብቶች መካከል የሚመደብ ነው። እንዲሁም ሰብአዊ መብቶች እርስ በእርስ ተደጋጋፊ፣ ተዛማጅ እና የማይነጣጠሉ ስለሆኑ ይህ መብት በራሱ መሠረታዊ የሆነ ሁሉም የሰው ልጆች ያለ ምንም ልዩነት ሊጠቀሙበት የሚገባ መብት ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች መከበርም እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚቆጠር መብት ነው። ስለሆነም ትምህርት የማግኘት መብት በአግባቡ አለመተግበር ሌሎች ሰብአዊ መብቶች እንዲጣሱ ምክንያት ይሆናል።

የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባህል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን ትምህርት የማግኘት መብትን በዝርዝር እና ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ የተነተነ ሕግ ነው ማለት ይቻላል። ይህ ቃልኪዳን በአንቀጽ 13/1 ላይ አባል ሀገራት ሁሉም ሰው ትምህርት የማግኘት መብት እንዳለው ዕውቅና እንደሰጡ የሚያሳይ ሲሆን መብቱ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎችም ይዘረዝራል። በዚህም መሠረት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ግዴታ እንደሆነ እና በነጻ መቅረብ እንዳለበት፤ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በአጠቃላይ ለሁሉም ክፍት፣ ተደራሽ እና በሂደትም በነጻ መደረግ እንዳለበት፤ እና የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ ችሎታን መሠረት አድርጎ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን፣ በሂደትም ያለክፍያ እንዲሰጥ መደረግ እንዳለበት ቃልኪዳኑ ደንግጓል። በተጨማሪም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ያልተማሩ ወይም ያላጠናቀቁ ሰዎች በተቻለ መጠን መሠረታዊ ትምህርት እንዲከታተሉ መበረታታት እንዳለባቸው፤ ትምህርቱም በስፋት መሰጠት እንዳለበት ይደነግጋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሀገራት የትምህርት ተቋማትን በየደረጃው እንዲያስፋፉ፣ ብቃት ያለው ነጻ የትምህርት ሥርዓት እንዲመሠርቱ እና የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ ያለማቋረጥ እንዲያሻሽሉ ይጠይቃል። በተጨማሪም ወላጆች እና አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን በመረጡት ትምህርት ቤት የማስተማር፤ እንዲሁም እንደ እምነታቸው ሃይማኖታዊ እና የሥነ ምግባር ትምህርቶችን እንዲማሩ የማድረግ መብት እንዳላቸው ደንግጓል። መንግሥት በግለሰቦችና በሌሎች አካላት የትምህርት ተቋማትን የመመሥረትና የመምራት ነጻነት ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደሌለበትም ይገልጻል። መንግሥት የሚሰጠው ትምህርት ያስቀመጣቸውን አስፈላጊ መመዘኛዎች ያሟላ መሆኑንም የመቆጣጠር ኀላፊነት አለበት። ከዚህ በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት ዘላቂ የልማት ግቦችም በግብ 4 ሥር ትምህርት ለዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋጽዖ አስቀምጧል።

ትምህርት የማግኘት መብት ይዘቶች ምንድን ናቸው?

የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ኮሚቴ በአጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 13 ላይ በሰጠው አስተያየት መሠረት ትምህርት የማግኘት መብት የሚከተሉት እርስ በእርስ ተያያዥነት ያላቸው አላባዎች አሉት።

  1. መገኘት (Availability):- ይህ የትምህርት የማግኘት መብት ይዘት ሀገራት በግዛታቸው ውስጥ በበቂ መጠን የትምህርት ተቋማት እና ፕሮግራሞች ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚጠይቅ ነው። ተቋማቱም አስፈላጊ የሆኑ ሕንፃዎች፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ፣ ተገቢው ስልጠና ያላቸው እና በቂ ደመወዝ የሚከፈላቸው መምህራን፣ የማስተማሪያ መሣሪያዎች እና የመሳሰሉት፤ እንዲሁም እንደስፈላጊነቱ ቤተመጽሐፍት፣ ተገቢ የሆኑ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች  (ኮምፒውተር፣ የግንኙነት መሠረት ልማቶች እና መሣሪዎች፣  ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ…) ሊኖራቸው ይገባል።
  2. ተደራሽነት:- ሀገራት በግዛታቸው ውስጥ የሚገኙ የትምህርት ተቋማትና ፕሮግራሞች ለማንኛውም ሰው ከአድልዎ በፀዳ መልኩ ተደራሽ መሆን አለባቸው ማለት ሲሆን፣ ሦስት ንዑስ አላባዎች/መገለጫዎች አሉት። እነዚህም:-
    • ትምህርት ለሁሉም በተለይም ተጋላጭ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ያለምንም አድልዎ ተደራሽ ማድረግ፤ 
    • አካባቢያዊ ተደራሽነት፦ ሰዎች ለትምህርት ብለው ከአካባቢያቸው ርቀው መጓዝ ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ በአካባቢያቸው ትምህርት እንዲያገኙ ማስቻል ነው። ይህንንም ለማድረግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ትምህርት መስጠት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።  
    • የኢኮኖሚ ተደራሽነት፦ ይህ መገለጫ የትምህርት ክፍያ የሰዎችን ዐቅም ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን እንዳለበት የሚያሳይ ነው።
  3. ተቀባይነት:- ይህ ይዘት የትምህርት ዓይነትና ይዘት፣ ሥርዓተ ትምህርቱንና የማስተማር ሥነ-ዘዴን ጨምሮ ለተማሪዎች እና እንደ ሁኔታው ለወላጆች ተስማሚና ተገቢነት ያላቸው፤ ባህልን ከግምት ውስጥ ያስገቡ እና ጥራታቸው የተጠበቀ መሆን እንዳለበት የሚያስገነዝብ ነው።
  4. ተስማሚነት፦ ይህ ይዘት ትምህርት ተለዋዋጭ የሆነውን የማኅበረሰብ እና የተማሪዎች ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆን እንዳለበት የሚያሳይ ነው። 

ትምህርት የማግኘት መብት ዓላማዎች ምንድን ናቸው? 

በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 26/2 እና የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን አንቀጽ 13 ሥር በግልጽ እንደተደነገገው፣  የትምህርት ዓላማ የሰውን ልጅ የተሟላ እድገት ለማራመድ እና የሰብአዊ መብቶችንና መሠረታዊ ነጻነቶችን ለማክበር የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር/ማገዝ ነው።  ከዚህ አንጻር ትምህርት የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ እድገት ማለትም አካላዊ፣ አእምሯዊ እና ሥነ-ልቦናዊ እድገት የማምጣት ዓላማ አለው። 

በተጨማሪም ትምህርት  በሕዝቦች፣ በዘሮች/በብሔሮች እና በሃይማኖቶች መካከል መግባባትን፣ መቻቻልን እና ወንድማማችነትን በማምጣት ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ሌላው የትምህርት መብት ግብ ነው።  ስለሆነም ትምህርት የሰውን ስብእና እና ክቡርነት ለማሳደግ በሚያስችል አቅጣጫ መመራት፤ ለሰብአዊ መብቶች እና መሠረታዊ ነጻነቶች የሚሰጠውን ከበሬታ የሚያጠናክር፤ ማንኛውም ሰው በነጻ ኅብረተሰብ ውስጥ ፍሬያማ ተሳትፎ እንዲኖረው የሚያስችል፤ በሁሉም ሕዝቦች፣ ዘሮች፣ ጎሳዎች ወይም ሃይማኖቶች መካከል መግባባትን፣ መቻቻልንና ወዳጅነትን የሚያጠናክር መሆን አለበት።

የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ኮሚቴ በአጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 13 ላይ በሰጠው አስተያየት ትምህርት ተጋላጭ የሚባሉትን የኅብረተሰብ ክፍሎች በማብቃት ረገድ እና የሕፃናትን፣ ሴቶችን እና ወጣቶችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ያስረዳል። ትምህርት ግለሰቦች ከድህነት እንዲላቀቁ እና በማኅበረሰቡ ውስጥ ሙሉ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ቁልፍ ሚና ይጫወታል። ስለሆነም ትምህርት አንድ ሀገር በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስክ ከፍተኛ እድገት ለማስመዝገብ ጭምር ቁልፍ አስተዋጽዖ ያበረክታል። በዚህም ምክንያት ትምህርት የማግኘት መብት በበርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች ዕውቅና አግኝቷል። (ከነዚህም መካከል  ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 26፤ የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 17፤ እንዲሁም በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት እና የሕፃናት መብቶች ስምምነትን መጥቀስ ይቻላል።) 

ትምህርት የማግኘት መብት በኢትዮጲያ ሕጎች ውስጥ ምን ይመስላል? 

ትምህርት የማግኘት መብት በኢትዮጲያ ሕጎች ውስጥ ዕውቅና የተሰጠው ሰብአዊ መብት ነው። ምንም እንኳን የኢትዮጲያ ሕገ መንግሥት ከላይ እንዳየናቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች በማያሻማ መልኩ በግልጽ ዕውቅና ባይሰጥም የሕገ መንግሥቱ የተለያዩ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ትምህርት የማግኘት መብት ዕውቅና እንደተሰጠው ያስረዳሉ። በተለይም የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 41 ስለ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ይደነግጋል። የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 4 እንደሚደነግገው መንግሥት የጤና፣ የትምህርት እና ሌሎች የማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ሀብት መመደብ አለበት። በተጨማሪም ሕገ መንግሥቱ በአንቀስ 90 ላይ ማኅበራዊ ዓላማዎች ሥር የሀገሪቱ ዐቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ መደረግ እንዳለበት የሚደነግግ ሲሆን፣ ትምህርቱም በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተጽዕኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሄድ እንዳለበት ይገልጻል። በተጨማሪም ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 9/4 ሥር እንዳስቀመጠው ከላይ የተዘረዘሩት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች የሀገሪቱ የሕግ አካል ናቸው።

ከሕገ መንግሥቱ እና ኢትዮጵያ ካጸደቀቻቸው ስምምነቶች በተጨማሪ ትምህርት የማግኘት መብት በሌሎች ትምህርት እና ስልጠና በሚመለከት የወጡ ሕጎች እና ፖሊሲዎች ዕውቅና የተሰጠው መብት ነው። በዚህ ረገድ በየካቲት ወር 2015 ዓ.ም. ላይ የወጣው አዲሱ የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ሊጠቀስ ይችላል። ይህ ፖሊሲ የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ፣ በዜጎች መካከል ያለውን እምነት እና መልካም ግንኙነት ለማዳበር፣ እንዲሁም የሕግ የበላይነትንና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ ትምህርት የሚኖረውን ከፍተኛ ሚና በመግቢያው ክፍል አስቀምጧል። በተጨማሪም ከፖሊሲው ዋና ዋና ዓላማዎች መካከል አንዱ ጥራት ያለው ትምህርት በተለይም ከቅድመ አንደኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ነጻና የግዴታ ትምህርት በተስማሚ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ለሁሉም በማዳረስ የግለሰብን አእምሯዊ፣ ማኅበራዊ፣ መንፈሳዊ እና መልካም እሴቶችን ማጎልበት እንደሆነ ያትታል።

ትምህርት የማግኘት መብት ተጣሰ የሚባለው መቼ ነው? 

መንግሥት ከላይ የተጠቀሱትን ግዴታዎቹን በአግባቡ ካልተወጣ ትምህርት የማግኘት መብት እንደተጣሰ ይቆጠራል። በተለይም በሰዎች መካከል አድልዎን በማበረታታት የሁሉንም ሰው እኩል የትምህርት ዕድል ተጠቃሚነትን ሊያጣብቡ የሚችሉ ሕጎችን ማውጣት፣ ወይም እንደዚህ ዓይነት ሕጎችን አለማሻሻል፣ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን አለመጠገን፣ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን አልያም በተለያዩ ምክንያቶች በመፈናቀል ውስጥ ያሉ ሰዎችን የትምህርት መብት አለማረጋገጥ/እንዲረጋገጥ ጥረት አለማድረግ ወዘተ የትምህርት መብትን የሚጥስ ነው። በተጨማሪም የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባህል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን አንቀጽ 13 ዓላማዎች ጋር ተቃራኒ የሆነ የትምህርት ሥነ-ዘዴ መጠቀም፤ የትምህርት ሥርዓቱ ከኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባህል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን ጋር የሚጣጣም መሆኑን የሚቆጣጠር ግልጽና ውጤታማ የክትትል ሥርዓት አለመዘርጋት፤ የግል ትምህርት ቤቶች እንዳይቋቋሙ ክልከላ መጣል፤ የግል ትምህርት ተቋማት በሕግ በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት እየሠሩ መሆኑን አለመከታተል፤ እና በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሕጎች መሠረት ከመንግሥት የሚጠበቁበትን ግዴታዎች አለመወጣት ትምህርት የማግኘት መብት ጥሰትን ያስከትላል።

Related posts

January 24, 2023August 28, 2023 Human Rights Concept
ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጠውን ትምህርት የመምረጥ መብት
September 6, 2023September 6, 2023 Human Rights Concept
ትምህርት የማግኘት መብት
April 26, 2023April 26, 2023 Human Rights Concept
ጤናማ እና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት
March 16, 2023August 28, 2023 Press Release
አዲስ አበባ፡ የከተማ አስተዳደሩ ባለሦስት እና አራት እግር (ባጃጅ) አነስተኛ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ላይ ያስቀመጠውን ሙሉ እገዳ በማንሳት ለችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያመቻች ይገባል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.