Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ኦሮሚያ: የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን ማጣራት እና ስለ ታሳሪዎች አያያዝ

May 24, 2020February 11, 2023 Press Release, ጋዜጣዊ መግለጫ

የሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ እና ሌሎችም መጠነ ሰፊ የጸጥታ ችግር ፣ የሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት ተከስቷል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አሳዛኝ ግድያ ተከትሎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎችም አንዳንድ ቦታዎች የተከሰተውን መጠነ ሰፊ የጸጥታ ችግር ፣ የሕይወት መጥፋት  እና የንብረት ውድመት በሚመለከት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከመነሻው ጀምሮ በቅርብ መከታተሉን የቀጠለ ሲሆን፤ እስከ አሁን የተካሄዱትና በመካሄድ ላይ ያሉት ዋና ሥራዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-

1. የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በፈጣን ምርመራ ማጣራትና መዘገብ

ምንም እንኳን የደረሰውን አደጋ በተመለከተ በተወሰነ መጠን በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንና ድርጅቶች እንዲሁም የፌዴራልና የክልል መንግሥት የተዘገበ ቢሆንም፤ ኢሰመኮ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የምርመራ ስልት ላይ የተመሰረተና በበቂ ማስረጃዎች የተደገፈ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አይነት በተገቢው መጠን የሚያጣራና የሚመዘግብ የባለሙያዎች ቡድን አዋቅሮ ወደ ሥራ አሰማርቷል፡፡

ምርመራው እስከ አሁን ድረስ በተደረገው ቅድመ ጥናት ሰፊ ችግር የተከሰተባቸው ተብለው በተለዩ 15 ቦታዎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሚካሄድ ሆኖ በተጨማሪም አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች መጠነኛ ችግር በተከሰተባቸው ወደ 40 የሚሆኑ ቦታዎች ላይም ስለ ደረሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አጠቃላይ መረጃ የሚሰበስብ ይሆናል፡፡ የምርመራው ውጤት የደረሰውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዓይነት፣ መጠን እና አዝማሚያ ለመለያት፣ የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ፣ የተጐዱ ሰዎች የሚካሱበትና መልሶ የሚቋቋሙበት እንዲሁም ይህን የመሰለ ጥሰት ደጋግሞ ከመከሰት ለመከላከል ስለሚያስችሉ እርምጃዎች ተገቢ ግብዓት እንደሚሆን እናምናለን፡፡ ስለ አደጋው ሁኔታ መረጃና ማስረጃ ያላቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች ለኮሚሽኑ ማሳወቃቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

2. ስለ እስረኞች አያያዝ ክትትል

አደጋውን ተከትሎ መንግሥት በወሰደው እርምጃ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል፡፡ በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ወይም የተከሰሱ ሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ በተመለከተ ኢሰመኮ ስልታዊ ክትትል በማድረግ ላይ ሲሆን፤ እስከ አሁን ድረስ እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ እስክንድር ነጋ እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነትን ጨምሮ ሌሎች ታሳሪዎችም የሚገኙበትን የእስር ሁኔታ በተከታታይ ተመልክቷል፡፡

በተለይም እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና እስክንድር በቀለ በመጀመሪያ ላይ ታስረው ይገኙ የነበረበትን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር ያለውን እስር ቤት፣ እንዲሁም አሁን የሚገኙበትን በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኘውን እስር ቤት በተጨማሪም በተለምዶ እንቁላል ፋብሪካ የሚባለው አካባቢ የሚገኘውን ጊዜያዊ የእስር ቤት ኮሚሽኑ ጐብኝቷል፣ ታሳሪዎችንና ኃላፊዎችንም አነጋግሯል፡፡

ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት ሰኔ 27 ቀን 2012 ዓ.ም. በአወጣው መግለጫና በተከታታይ ይሰጥ በነበረው የሚዲያ ማብራሪያ ላይ እንደተገለጸው በተለይ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር የሚገኘው ታሳሪዎቹ የሚገኙበት አካባቢና ክፍሎቹ በአንጻራዊነት እጅግም ያልተጨናነቁ፣ የተፈጥሮና የኤሌክትሪክ ብርሃን ያላቸው፣ የመታጠቢያና የንጽሕና ቤቶቹ ፅዳታቸው የተጠበቀና በአጠቃላይ አነጋገር የተቀባይነት ደረጃ ያላቸው መሆኑን ያስታውሳል፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽኑ በእነ አቶ እስክንድር ነጋ የእስር አያያዝ ላይ እንዲሻሻል ምክረ ሀሳብ የሰጠባቸው ጉዳዮች ተግባራዊ መደረጋቸውን፣ እንዲሁም ከነገሩ ሁኔታ አንጻር በዋስትና መብት ሊለቀቁ ስለሚገባቸው የተወሰኑ ታሳሪዎች የሰጠው ምክር ሃሳብም በሚመለከታቸው የፍትሕ አስተዳደር አካላት ተግባራዊ መደረጉን በመልካም እርምጃነቱ እውቅና ይሰጣል፡፡

አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ስንታየሁ ቸኰልን ጨምሮ ስድስት ታሳሪዎች አሁን የሚገኙበት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኘው እስር ቤትም ንፅሕናው የተጠበቀ፣ የተፈጥሮና የኤሌክትሪክ ብርሃን የሚያገኝ፣ ታሳሪዎቹ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ከቤተሰብ አቅርቦት የሚቀበሉበትና ለመተያየት የሚችሉበት፣ በአጠቃላይ አነጋገር ተቀባይነት ደረጃ ያለው ሲሆን፤ በተወሰነ መልኩ ከወቅቱ የአየር ጸባይና ከሕንጻው ባሕሪ የተነሳ የመቀዝቀዝ ጠባይ ያለው በመሆኑ ቅዝቃዜውን ለመቀነስ የሚያስችል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ተመልክተናል፡፡

በዚህ እስር ቤት ካሉት ታሳሪዎች ውስጥ አቶ ሃምዛ ቦረና እና አቶ ሸምሰዲን ጣሃ የሕክምና ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን አቶ ሃምዛ ቦረና ከኮሚሽኑ ጉብኝት ማግስት ወደ ሕክምና የሄዱ ሲሆን አቶ ሸምሰዲንም በአፋጣኝ የሕክምና ጉብኝት እንደሚያገኙ ተረጋግጦልናል፡፡

በዚህ የእስር ቦታ በአጠቃላይ አነጋገር እና በአብዛኛዎቹ ታሳሪዎች እንደተገለጸልን ተገቢ ያልሆነ የእስር አያያዝ አለመኖሩንና ፖሊሶች በተገቢው የሙያ ሥነ ምግባር የሚሰሩ መሆኑን ተረድተናል፡፡

በሌላ በኩል ከታሳሪዎች የቀረቡትን መጠነኛ ቅሬታዎች ውስጥ ከቤተሰብ ጋር በተገቢው መጠን ተቀራርቦ ለመተያየት አለመቻሉ፣ የክፍሎቹ መቀዝቀዝ፣ የጸሐይ መቀበያ ጊዜ ማጠር፣ የመብራት መቋረጥ፣ የታሳሪዎች ለረጅም ጊዜ ለብቻ መቆየት የመሰሉ ችግሮች ሊሻሻሉ ስለሚችሉበት መንገድ ኮሚሽኑ ከኃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ያደረገ ሲሆን አፈጻጸሙንም በቅርበት ይከታተላል፡፡

በተለምዶ እንቁላል ፋብሪካ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ታሳሪዎች ውስጥ የኦ.ኤ.ም.ኤን (OMN) ጋዜጠኞች የነበሩ አቶ ጉዬ ዋርዮ እና አቶ ሙሀመድ ሲራጅ፣ የኦፌኮ አባል አቶ ደጀኔ ጣፋ እንዲሁም ሶስት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ አገር ዜጐች እና በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠለፋ ጉዳይ ተጠርጥረው የተከሰሱ ታሳሪዎችን ጨምሮ ሌሎች እስረኞችንም ኮሚሽኑ ጐብኝቷል፡፡

አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች በእስር ወቅትም ሆነ ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያው ከመጡ ጀምሮ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንዳልተፈጸመባቸው፣ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያው ውስጥ የእስር አያያዙ በአጠቃላይ አነጋገር መልካም ቢሆንም በተለይ ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት አንጻር ከፍተኛ አስጊ ሁኔታ መኖሩን፣ የንፅሕና መጠበቂያና የመከላለያ ቁሶች አቅርቦት እጥረት መኖሩን፣ በአንድ ክፍል ውስጥ ብዙ ሰዎች በመኖራቸው እያደገ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነት ሥጋት እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም ከቤተሰብ መገናኘትን በሚመለከት የተወሰኑ ታሳሪዎች ገና ከቤተሰብ ያልተያዩ መሆኑንና የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ታሳሪዎችም በውጭ አገር የሚገኙ ቤተሰቦቻቸውን ገና በስልክ ለማነጋገር ዕድል አለማግኘታቸውን ገልጸውልናል፡፡ እነዚሁ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ታሳሪዎችም ዘግይቶም ቢሆን ከአገራቸው ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር መገናኘት መቻላቸውን አረጋግጠውልናል፡፡

አንድ ታሳሪ በእስር ወቅት ፖሊስ ተገቢ ያልሆነ እንግልት እንደፈጠረባቸውና በጥፊና በእርግጫ  እንደመታቸው እንዲሁም ሁለት ታሳሪዎች በኦሮሚያ ባሕል ማዕከል ውስጥ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት አጠቃላይ ሁኔታው አስፈሪና አስጨናቂ እንደነበር፣ እንዲሁም በቁጥጥር ስር በዋሉበት የመጀመሪያው ቀን ምሽትና አዳር ያለ ምግብ፣ ውሃ እና የብርድ ልብስ ኮሪደር ላይ ለማሳለፍ መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በአንጻሩ በቁጥጥር ስር ከዋሉና በተለይም አሁን ወደሚገኙበት ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ከመጡ በኃላ የእስር አያያዙ የተሻሻለ መሆኑን፣ ፖሊሶቹም በከፍተኛ የሙያ ሥነ ምግባር የሚሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በተማሪዎች እገታ ጉዳይ ተጠርጥረው የታሰሩት ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ በኦሮሚያ ክልል ደምቢዶሎ ከተማ ታስረው በቆዩበት ወቅት የተማሪዎቹን ጠላፊዎች ታውቃላችሁ በሚል ጥርጣሬ በተደጋጋሚ እንደተደበደቡ፣ እንደተገረፉ፣ በሽጉጥ የማስመሰል ግድያ (Mock Execution) እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን፤ በአንጻሩ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ከመጡ ጀምሮ ምንም ዓይነት ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንዳልተፈጸመባቸውና ጠቅላላ የእስር አያያዛቸውም መልካም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ ሁለት ታሳሪዎች ፍርድ ቤት እንዲለቀቁ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም እስከ ጉብኝቱ ቀን ድረስ ገና አለመለቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ እነዚህን ሁሉ ጉዳዮችና በተለይም የተወሰኑት ታሳሪዎች በኦሮሚያ ክልል ደምቢዶሎ ከተማ እስር ወቅት ተፈጽሟል የተባለውን ድብደባ እና የማሰቃየት ድርጊት የሚያጣራ ይሆናል፡፡

በአብዛኛዎቹ ታሳሪዎች የተነሳው ሌላው ተደጋጋሚ ቅሬታ የወንጀል ምርመራ የሚወስደው ጊዜ፣ ብዙ ታሳሪዎች ገና ቃላቸውን ያልሰጡና መርማሪ ፖሊስ ያላናገራቸው መሆኑ እና በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ እንደተገነዘበው የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር አካላት እጅግ ውስን በሆነ የሰው እና የፋይናንስ አቅም በርካታ ጉዳዮችን በማጣራት ከፍተኛ የሥራ ጫና ያለባቸው ቢሆንም በተቻለ መጠን የምርመራ ስራውን ማቀላጠፍ እና በዋስትና መብት ሊለቀቁ የሚገባቸውን ታሳሪዎች በአፋጣኝ መለየት ልዩ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡

በሌላ በኩል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ታሳሪዎች በሚመለከት ኮሚሽኑ በቅርቡ ለመመልከት በዝግጅት ላይ ያለ ቢሆንም፤ ብዙ ታሳሪዎች ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ በተሟላ ሁኔታ ያለወቁ በመሆኑ ሁሉም ታሳሪዎች ለቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ በስልክ እንዲያስታውቁ እንዲደረግ ምክረ ሀሳብ ሰጥቷል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡

በተለይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ብዙ አባሎቻቸው እና የፖለቲካ ፖርቲዎቹ አመራሮች እንደታሰሩና ያሉበትን ቦታና ሁኔታ ለማወቅ አለመቻላቸውን ለኮሚሽኑ ያሳወቁ ሲሆን፤ ሁሉም የፖሊስ ኮሚሽን አባላት በቁጥጥር ስር የሚያደርጓቸውን ታሳሪዎች ወዲያውኑ ለቤተሰባቸው ያሉበትን ቦታ በስልክ እንዲያሳውቁ ሊደረጋ እንደሚገባ ኮሚሽኑ ያሳስባል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የታሳሪዎች ጉዳይን በሚመለከት በሰጡት አስተያየት “አሁን በአለው የሰላምና መረጋጋት እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ፤ ፖሊስና ዐቃቤ ሕግ በቅድሚያ ትኩረት ሊያከናውኑ የሚገባው ጉዳይ፤ ሁሉም ታሳሪዎች ቤተሰቦቻቸውን በስልክ በማናገር የአሉበትን ቦታ ማሳወቃቸውን ማረጋጥ እና በተፋጠነ ምርመራ በዋስትና መብት ወይም በነጻ ሊፈቱ የሚገባቸውን ታሳሪዎች በመለየት በአፋጣኝ መለቀቃቸውን ማረጋገጥ ነው” ብለዋል፡፡        

Related posts

May 22, 2022October 5, 2022 EHRC Quote
በተለያዩ አካባቢዎች በመፈጸም ላይ ያሉ የጋዜጠኞች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎችና የሌሎች ሰዎች እስሮች
February 15, 2023August 28, 2023 EHRC Quote
ኢሰመኮ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተደረጉ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ተከታዮች እና የተለያዩ ሚዲያ አባላት እስር በእጅጉ እንደሚያሳስብ ገለጸ
March 9, 2021February 11, 2023 Press Release
አዲስ አበባ: ከትግራይ ክልል ሁኔታ ጋር በተገናኘ የታሰሩ ተጠርጣሪዎች አያያዝ
October 30, 2020February 11, 2023 Press Release
ስለ እስረኞች አያያዝ ክትትል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.