ዓለም አቀፉ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 7
ማንም ሰው ለማሰቃየት ተግባር ወይም ጭካኔ ለተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም ክብርን ለሚያዋርድ አያያዝና ቅጣት ሊጋለጥ አይገባም።
ማሰቃየት እና ሌሎች ጭካኔ የተሞላባቸው፣ ኢ-ሰብአዊና አዋራጅ አያያዞችንና ቅጣቶችን ለማስቀረት የተደረገ ስምምነት፤ አንቀጽ 2
ማንኛውም ልዩ ሁኔታ፣ ጦርነት ወይም የጦርነት ሥጋት፣ የውስጥ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ወይም ሌላ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ፤ ከበላይ አካል ወይም ከመንግሥት ባለስልጣን የሚተላለፍ ትእዛዝ ለማሰቃየት ተግባር ሕጋዊ መከላከያ ሊሆኑ አይችሉም።