የአፍሪካ ወጣቶች ቻርተር፣ አንቀጽ 17(ሀ) እና (ሠ)
ወጣቶች ሰላምን እና ከሁከትና ብጥብጥ ነጻ መሆንን በማጎልበት ረገድ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና እንዲሁም በሁከትና ብጥብጥ፣ በትጥቅ ግጭት እና በጦርነት ውስጥ መሳተፋቸው የሚያስከትለውን ዘላቂ የአካልና የሥነ-ልቦና ጉዳት በመገንዘብ፣ አባል ሀገራት፦
- የእርስ በእርስ የባህል ትውውቅን፣ የሥነ ዜጋ ትምህርትን፣ የመቻቻል ባህልን፣ የሰብአዊ መብቶች ትምህርትና ዴሞክራሲን፣ በባህል፣ በብሔር እና በሃይማኖት ብዝኃነት መከባበርን፣ የውይይት እና ትብብር ጠቀሜታን፣ የኃላፊነት ስሜትን፣ አጋርነትን እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ዋጋ በመስጠትና በማሳደግ የወጣቶችና የወጣት አደረጃጀቶች በሰላም ግንባታ፣ በግጭት መከላከል እና በግጭት አፈታት ረገድ ያላቸውን ዐቅም ማሳደግ አለባቸው፤
- ወጣቶችን ጨምሮ በትጥቅ ግጭት የተጎዱ እና የተፈናቀሉ ሲቪል ሰዎችን ለመጠበቅ የሚቻላቸውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ።