የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ስደተኞች በግጭት ወቅትም የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አላቸው፡፡

የተ.መ.ድ. የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መመሪያ መርሆች፣ መርህ 10

በማንኛውም ሁኔታ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ወይም መሳተፋቸውን ባቆሙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ላይ ጥቃቶችን በተለይም፤ ቀጥተኛ የሆነ ወይም የጅምላ ጥቃት ወይም ሌሎች ጥቃቶች፣ ረሀብን ለጦርነት ዓላማ ማዋል፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወታደራዊ መገልገያዎችን ከጥቃት ለማዳን ወይም ለመደበቂያነት መገልገል፣ በመጠለያቸው ወይም በማረፊያቸው ላይ ጥቃት ማድረስ የተከለከለ ነው፡፡

በጦርነት ግጭት ጊዜ ስደተኞችን ማጥቃት፣ ማፈናቀል፣ እንዲሰወሩ ማድረግ ወይም በአግባቡ አለመያዝ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸም የጦርነት ወንጀል ነው፡፡ (የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ፣ አንቀጽ 270(ቸ))