በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍን አስመልክቶ የተደረገ የአፍሪካ ኅብረት ስምምነት (የካምፓላ ስምምነት)፣ አንቀጽ 11 (1)፣ (2)
- ተዋዋይ ሀገራት በዘላቂነት እና ደኅንነትንና ክብርን በጠበቀ መልኩ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የመመለስ፣ ከአካባቢ ማኅበረሰብ ጋር ተዋሕዶ የመኖር ወይም ወደ ሌላ ቦታ የማስፈር መፍትሔዎችን ለማመቻቸት አጥጋቢ የሆኑ ሁኔታዎች በማበረታታትና በመፍጠር ለመፈናቀል ችግር ዘላቂ መፍትሔዎችን ማፈላለግ አለባቸው፡፡
- የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የመመለስ፣ ከአካባቢ ማኅበረሰብ ጋር ተዋሕዶ የመኖር ወይም ወደ ሌላ ቦታ የመስፈር አማራጮችን ነጻ ሆነውና በመረጃ ተደግፈው መምረጥ እንዲችሉ ተዋዋይ ሀገራት በእነዚህና ሌሎች አማራጮች ዙሪያ ሊያማክሯቸው እና ዘላቂ መፍትሔዎችን በመፈለግ ሂደት መሳተፍ እንዲችሉ ሁኔታዎችን ሊያመቻቹላቸው ይገባል፡፡