ም አቀ የሰብአዊ መብቶች መግጫ፣ አንቀጽ 26 

  • ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው፡፡ ቢያንስ የአንደኛ ደረጃና መሠረታዊ ትምህርት በነጻ ሊሰጥ ይገባል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ግዴታ ሊሆን ይገባል።
  • ትምህርት ለሰው ልጅ የተሟላ የስብእና እድገትን ለማምጣት እና የሰብአዊ መብቶችንና መሠረታዊ ነጻነቶች መከበርን ለማጠናከር ያለመ መሆን አለበት፡፡ ትምህርት በሁሉም ሀገራት፣ በተለያዩ ዘሮችና ሃይማኖቶች መካከል መግባባትን፣መቻቻልን እና ወዳጅነትን ሊያጎለብት ይገባል።