(መግቢያ) 

እ.ኤ.አ. በ1948 የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፋዊ መግለጫ ለሁለም ሕዝቦችና ሀገራት የጋራ መመሪያ እና የስኬት መለኪያ እንዲሆን አውጇል፡፡ ለዚህም በምክንያትነት ከተቀመጡት መሃከል:-

  • የተባበሩት መንግሥታት አባል ሀገራት ሕዝቦች በመሠረታዊ የሰብአዊ መብቶች፣ በሰውነት ክብር እና ልዕልና እና በጾታዎች እኩልነት ላይ ያላቸውን ጽኑ እምነት በቃል ኪዳኑ ውስጥ በድጋሚ በማረጋገጣቸው እና ሰፋ ባለ የነጻነት ሁኔታ የማኅበራዊ እድገትና የተሻለ የኑሮ ደረጃን ለማረጋገጥ በመወሰናቸው፤ እንዲሁም
  • ከተባበሩት መንግሥታት ጋር በመተባበር አባል ሀገራት ሰብአዊ መብቶችና መሠረታዊ ነጻነቶች በመላው ዓለም እንዲከበሩና በተግባር እንዲተረጎሙ ለማድረግ ቃል በመግባታቸው፤ ይህ ቃል ኪዳን ሙሉ በሙሉ ግቡን እንዲመታ ስለ እነዚህ መብቶችና ነጻነቶች የጋራ ግንዛቤ እንዲኖር ማድረግ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡

የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፋዊ መግለጫውን 75 ዓመት ዘንድሮ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. እናከብራለን።

#ሰብአዊመብቶች75