ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓላማዎችና መርሆዎች መሀል አንዱ፤
ዓለም አቀፋዊ የሆኑ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊ ወይም የሰብአዊነት ተፈጥሮ ያላቸውን ችግሮችን ለመፍታት፤ እንዲሁም የሰብአዊ መብቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች መስፋፋትን እና በዘር፣ በጾታ፣ በቋንቋ ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ ለሁሉም ሰው እንዲከበሩ የሚያስችል ዓለም አቀፍ ትብብርን ማረጋገጥ ነው፡፡ (የተ.መ.ድ. ቻርተር፣ አንቀጽ 1)
የተ.መ.ድ. ቻርተር እ.ኤ.አ. በ1945 ከጸደቀ 77 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
ኢትዮጵያ በሳን ፍራንሲስኮ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፍ ድርጅት ጉባኤ ላይ ከተሳተፉት አራት የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ነበረች፡፡