በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 12 (2)

  • አባል ሀገራት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ነጻ አገልግሎት እንዲሁም በእርግዝና እና ጡት ማጥባት ጊዜ በቂ ምግብ በመስጠት ከእርግዝና፣ ወሊድ እና ድኅረ ወሊድ ጊዜ ጋር በተያያዘ ሴቶች ተገቢውን አገልግሎት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 35 (9)

  • ሴቶች በእርግዝና እና በወሊድ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመከላከል እና ጤንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት፣ መረጃ እና ዐቅም የማግኘት መብት አላቸው።