የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 10 (1) እና (2) (ሀ) (ለ) (ሠ) 

  • ሴቶች በሰላም የመኖር እንዲሁም ሰላምን በማስፋፋትና በማስጠበቅ ሥራዎች ላይ የመሳተፍ መብት አላቸው። 
  • አባል ሀገራት፦ 
    • ለሰላም እና ለሰላም ባህል በሚሰጡ የትምህርት መርኃ ግብሮች፣ 
    • በአካባቢ፣ በሀገር፣ በቀጠና፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉ የግጭት መከላከል፣ አስተዳደር እና አፈታት መዋቅሮች እንዲሁም የአሠራር ሂደቶች፣ 
    • በሁሉም የድኅረ ግጭት የመልሶ ግንባታ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ዕቅድ፣ ዝግጅት እና ትግበራ ዘርፎች የሴቶችን ከፍ ያለ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ተገቢውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ አለባቸው።