ሁሉንም ሰው ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የወጣ ዓለም አቀፍ ስምምነት፣ አንቀጽ 24 

ማናቸውም አስገድዶ መሰወር የተፈጸመበት ሰው ቤተሰቦች (ሌሎች ተጎጂዎች) አስገድዶ መሰወር የተፈጸመበትን ሁኔታ፣ ምርመራው ያለበትን ደረጃ እና ያስገኘውን ውጤት፣ እንዲሁም የተሰወረውን ሰው እጣፋንታ በተመለከተ እውነቱን የማወቅ መብት አላቸው።

አባል ሀገራት የተሰወሩ ሰዎችን ለመፈለግ፣ ያሉበትን ለማወቅ/ለማሳወቅ እና ለመልቀቅ፤ ሞት በተከሰተ ጊዜ ደግሞ አስከሬናቸው ያለበትን ለማወቅ/ለማሳወቅ እና በክብር እንዲመለስ ለማድረግ ማናቸውንም ተገቢ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል።