የአፍሪካ የሰዎች እና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የአረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 9
አባል ሀገራት፦
- አረጋውያን ሴቶች ከጥቃት፣ ከወሲባዊ ጥቃት እንዲሁም በጾታ ላይ ከተመሠረተ መድልዎ መጠበቃቸውን ማረጋገጥ፤
- አረጋውያን ሴቶች ከንብረት እና መሬት መብቶች ጋር ከተያያዙ በደሎች መጠበቃቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሕጎችን ማውጣት እና ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ፤ እንዲሁም
- የአረጋውያን ሴቶችን የውርስ መብት ለመጠበቅ ተገቢውን ሕግ ማውጣት አለባቸው።