የአፍሪካ የሰዎች እና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር፣ አንቀጽ 24

  • ሁሉም ሕዝብ ለእድገቱ አመቺ የሆነ አጠቃላይ ተስማሚነት ያለው አካባቢ የማግኘት መብት አለው።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 44

  • ሁሉም ሰዎች ንጹሕና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው።
  • መንግሥት በሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች ምክንያት የተፈናቀሉ ወይም ኑሯቸው የተነካባቸው ሰዎች ሁሉ በመንግሥት በቂ እርዳታ ወደሌላ አካባቢ መዘዋወርን ጨምሮ ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ወይም ሌላ አማራጭ ማካካሻ የማግኘት መብት አላቸው።