Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት

April 28, 2023August 28, 2023 Explainer

ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ መብት ሲባል ምን ማለት ነው? ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ መብት ጋር የተገናኙ ግዴታዎች ምንድን ናቸው?

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Download Print

ማንኛውም ሠራተኛ ለጤናው እና ለደኅንነቱ ምቹ የሆነ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት ያለው መሆኑ በተለያዩ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ሕጎች ላይ ተደንግጎ ይገኛል። ሆኖም ሠራተኞች ሥራቸውን የሚያከናውኑበት የሥራ ሁኔታ ለጤናቸው እና ለደኅንነታቸው ተስማሚ አለመሆን እንዲሁም ለሠራተኞቹ መቅረብ ያለባቸው የተለያዩ የሥራ መሣሪያዎች ወቅታቸውን እና ጥራታቸውን ጠብቀው አለመቅረብ የተነሳ ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብታቸውን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም እንዳይችሉ እያደረጓቸው ስለመሆኑ ኢሰመኮ ከዚህ በፊት ባከናወነው የሰብአዊ መብቶች ክትትል አረጋግጧል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሙያ አደጋዎችን እና በሽታዎችን መከላከልን ለማበረታታት በማሰብ በየዓመቱ ሚያዝያ 20 ቀን የሥራ ላይ ደኅንነት እና ጤንነት ቀን ታስቦ ይውላል። በዚህም ዓመት “ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ አካባቢ እንደ መሠረታዊ መርሕ እና የሥራ ላይ መብት” (Safe and healthy working environment as a fundamental principle and right at work) በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የሥራ ላይ ደኅንነት እና ጤንነት ቀን ምክንያት በማድረግ ይህ ማብራሪያ ተዘጋጅቷል።

1. ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ መብት ሲባል ምን ማለት ነው?

ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ መብት ያለ አድሎ በማንኛውም የኢኮኖሚ ዘርፍ እና የቅጥር አይነት ለሚሠሩ ሠራተኞች የተሰጠ ከፍትሐዊ እና ምቹ የሥራ ሁኔታዎች መብት መሠረታዊ ገጽታዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከሌሎች መብቶች በተለይም የአካላዊ እና አዕምሯዊ ጤና መብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው። ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) “ጤና” ለሚለው ቃል የሰጠው ትርጉም ከበሽታና ከጉዳት ነጻ ከመሆን ባለፈ አካላዊ እና አእምሯዊ ደኅንነትን ያጠቃልላል።

ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ /የሙያ ደኅንነት እና ጤንነት/ በዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች፣ የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) ስምምነቶች እና የውሳኔ ሐሳቦችን ጨምሮ በተዛማጅ የዓለም አቀፍ የሕግ ሰነዶች እንዲሁም በሀገር ውስጥ ሕጎች ዕውቅና ያገኘ ሰብአዊ መብት ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ቃል ኪዳን፣ የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) የሙያ ደኅንነት እና የጤንነት ስምምነት ቁጥር 155፣ የሙያ ደኅንነትና ጤንነት ስምምነት 155 ፕሮቶኮል 2002 እና የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በዋነኝነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

እንዲሁም የሙያ ደኅንነት እና ጤንነት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2015 ካስቀመጣቸው የዘላቂ ልማት ግቦች ጋር የተሳሰረ ሲሆን በተለይም በግብ 8 ሥር ተካቶ ይገኛል፡፡ መብቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ገጽታ ያለው ሲሆን፣ አምራች ኃይልን ከጉዳት ይከላከላል፤ ምቹ የሥራ ሁኔታ በመፍጠር የሥራ ቅልጥፍናን፣ ጥራትን እንዲሁም ምርታማነትን በመጨመር ለዘላቂ ልማት አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡

2. ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ መብት ዙሪያ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሕግ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው?  

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ቃል ኪዳንን እና የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) የሙያ ደኅንነት እና ጤንነት ከተመለከቱ 15 ስምምነቶች መካከል አንዱን የሙያ ደኅንነት እና የጤንነት ስምምነት ቁጥር 155ን ያጸደቀች ሲሆን በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 42(2) እንደተመለከተውም ጤናማና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብትን ደንግጋለች። ከሕገ መንግሥቱ በተጨማሪ ለመብቱ ጥበቃ የሚሰጡ ሌሎች ሕጎችም ይገኛሉ። እነዚህም የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010፣ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና የሙያ ደኅንነት እና ጤንነት አጠባበቅ መመሪያ፣ ለወጣት ሠራተኞች የተከለከሉ ሥራዎች ዝርዝር እንደገና ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 813/2013፣ ለሴት ሠራተኞች ከባድ ወይም ለጤና ጎጂ የሆኑ ወይም የመውለድ ሁኔታን የሚያውኩ ሥራዎችን እንደገና ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 811/2013 እንዲሁም የሙያ ደኀንነትና ጤንነት ኮሚቴ ስለሚቋቋምበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 834/2014 እና ተከታይ መመሪያዎቹ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሥራ ቦታዎችና ሠራተኞች ከሥራ ላይ አደጋዎች እና በሥራ ምክንያት ከሚመጡ በሽታዎች የተጠበቁ ሆነው ማየትን አላማው ያደረገ ብሔራዊ የሙያ ደኅንነት እና ጤንነት ፖሊሲ እና ስትራቴጂም አላት፡፡

3. ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ መብት ጋር የተገናኙ ግዴታዎች ምንድን ናቸው?

3.1 የመንግሥት ግዴታዎች

ደኅንነቱ እና ጤንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት እንደማንኛውም ሰብአዊ መብቶች ሦስት ዓይነት ግዴታዎችን በመንግሥት ላይ የሚጥል ሲሆን እነዚህም የማክበር፣ የመጠበቅ እና የማሟላት ግዴታዎች ናቸው።

የማክበር ግዴታ መንግሥት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሠራተኞች መብታቸውን እንዳይጠቀሙ ከሚያደርግ ጣልቃ ገብነት በመቆጠብ መብቱን እንዲያከብር ግዴታ የሚጥልበት ሲሆን ይህ ግዴታ በመንግሥት ባለቤትነት ወይም በመንግሥት አስተዳደር ሥር ያሉ ድርጅቶችን ጨምሮ መንግሥት አሠሪ በሚሆንበት ጊዜ እጅግ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ መንግሥት በድርጊቱ ወይም ሊያደርግ ከሚገባው ድርጊት በመቆጠቡ ሳቢያ በሥራ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችንና በሽታዎችን መከላከል እና የእርምት እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል።

የማስከበር ግዴታ መንግሥት የግል ዘርፍ አሠሪዎችና ድርጅቶች (ሦስተኛ ወገኖች) የሠራተኞችን ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታዎችን የማግኘት መብት እንዳይጥሱ እንዲሁም ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግ ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስድ  ያለበትን የማስከበር ግዴታ የሚመለከት ነው። ይህም ውጤታማ የሆኑ ሕጎች እና ፖሊሲዎችን በመጠቀም ጥሰትን ለመከላከል፣ ለመመርመር፣ ለመቅጣት እና ለማረም የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድን እንዲሁም የሕግ ማእቀፎችን በቂነትና ውጤታማ በሆነ መንገድ መፈጸማቸውን ማረጋገጥን ይጨምራል።

የማሟላት ግዴታ መንግሥት ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታዎችን የማግኘት መብት ሙሉ በሙሉ እውን መሆኑን ለማረጋገጥ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወስድ ይጠይቃል።  ይህም በኅብረት ስምምነት/ድርድር እና በማኅበራዊ ውይይት አማካኝነት መብቱን ለማመቻቸት፣ ለማስፋፋት እና ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ያካትታል።

3.2 አሠሪ እና የአሠሪ ማኅበራት

የንግድ ድርጅቶች መጠናቸው፣ ዘርፋቸው፣ ባለቤትነታቸውና መዋቅራቸው ምንም ይሁን ምን፣ ማንኛውንም ጥሰት በማስወገድ እና ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቃል ኪዳን ጋር ለሚጣጣሙ ሕጎች በመገዛት መብቱን የማክበር ኃላፊነት አለባቸው።  የአሠሪዎች ሚና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሰነዶች ተካተው የሚገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በአንቀጽ 12(5) እና 92 መሠረት ከሥራው ጋር በተያያዘ የሠራተኛውን ደኅንነትና ጤንነት ለመጠበቅና ከአደጋ ለመከላከል የሚያስፈልጉትን እርምጃዎችን ሁሉ እንዲወስድ በአሠሪው ላይ ግዴታ ያስቀምጣል።

በአሠሪዎች ሊወሰዱ ከሚገባቸው እርምጃዎች መካከል ሠራተኞች የሚሠሩት ሥራ ሊያስከትልባቸው ስለሚችለው አደጋ እንዲሁም በጤንነት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለማስወገድ ስለሚያስፈልገው ጥንቃቄ ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር፣ የአደጋ ተከላካይ ሠራተኛ መመደብ፣ የሙያ ደኅንነትና ጤንነት ኮሚቴ ማቋቋም፣ ለሠራተኞች የአደጋ መከላከያ መሣሪያ ልብስና ሌሎች ቁሳቁሶችን ማቅረብና ስለአጠቃቀሙም መመሪያ መስጠት፣ በሥራ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችንና አደጋዎችን መመዝገብ ይገኙበታል። እንዲሁም እንደሥራው ጠባይ አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች በራሱ ወጪ የጤና ምርመራ እንዲካሄድላቸውና በአደገኛ ሥራ ላይ የሚሠሩ ሠራተኞችም እንደአስፈላጊነቱ የጤና ምርመራ እንዲደረግላቸው ማድረግ፣ የድርጅቱ የሥራ ቦታና ግቢ በሠራተኞች ደኅንነትና ጤንነት ላይ አደጋ የማያስከትል መሆኑን ማረጋገጥ እና በድርጅቱ ልዩ ልዩ የሥራ ሂደት በሚገኙ ፊዚካላዊ፣ ኬሚካላዊ፣ ባዮሎጂካዊ፣ ኢርጎኖሚካዊና ሥነ ልቦናዊ ምንጮችና ምክንያቶች ሳቢያ በሠራተኞች ደኅንነትና ጤንነት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግን ያጠቃልላል ።

አሠሪ እነዚህን ግዴታዎች ባለመወጣት የሠራተኛው ደኅንነት እና ጤና ላይ አደጋ ሊያደርስ በሚችል አኳኋን እንዲሠራ ካደረገ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 14(1(ሠ)) መሠረት አሠሪው ሕገወጥ ተግባር እንደፈጸመ ይቆጠራል።

3.3 ሠራተኞችና የሠራተኛ ማኅበራት

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በአንቀጽ 93 እና 94 እንደ አሠሪዎች ሁሉ የሠራተኞችን ግዴታዎችንም ደንግጓል። የሠራተኞችን ደኅንነትና ጤንነት ለመጠበቅ የሚወጡትን የሥራ ደንቦች በማዘጋጀት መተባበር እና በሥራ ላይ ማዋል፣ በድርጅቱ ወይም በድርጅቱ መሣሪያዎች ላይ የሠራተኞቹን ደኅንነትና ጤንነት የሚጎዳ ጉድለት ሲያገኝ፣ የሚደርሰውንም ማንኛውም አደጋ ወዲያውኑ ለአሠሪው ማሳወቅ፣ አደጋ ሊያደርስ ይችላል ብሎ ለማመን ምክንያት ያለውንና በራሱ ሊያስወግደው ያልቻለውን ማንኛውንም ሁኔታ እንዲሁም በሥራ ሂደት ወይም ከሥራ ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ በጤንነት ላይ የደረሰን አደጋ ወይም ጉዳት ለአሠሪው ማሳወቅ፣ የራሱን ወይም የሌሎች ደኅንነትና ጤንነት ለመጠበቅ የተሰጡትን የአደጋ መከላከያዎች፣ የደኅንነት መጠበቂያ መሣሪያዎችና ሌሎች መሣሪያዎችን በትክክል ጥቅም ላይ ማዋል፤ እንዲሁም አሠሪው ወይም ኃላፊነት የተሰጠው ባለሥልጣን ያወጣውን ወይም የሰጣቸውን የደኅንነትና ጤንነት መጠበቂያ መመሪያዎች ማክበር ይገኙበታል፡፡

ከመንግሥት፣ ከአሠሪ እና ከሠራተኛ በተጨማሪ የአሠሪ እና ሠራተኛ ማኅበራት፣ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን፣ ከፍተኛ የትምህርትና ምርምር ተቋማት እንዲሁም የሲቪክና የሙያ ማኅበራት ግንዛቤ በመፍጠር፣ የሙያ ደኅንነት እና ጤንነት ጉዳዮች በኅብረት ስምምነቶች እንዲካተቱ በማድረግ፣ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት፣ ጥናቶችን በማከናወን እንዲሁም ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ ለመብቱ ተግባራዊነት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ አካላት ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ጤናማ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ መብትን ለማሟላት ብሎም በመከላከል መርሕ ላይ የተመሠረተ የሙያ ደኅንነት እና ጤንነት ባህል ለመገንባት የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) የሙያ ደኅንነትና ጤንነት ስምምነት 155 ፕሮቶኮል 2002ን ጨምሮ በዘርፉ ያሉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በማጽደቅ ሥራ ላይ ማዋል እና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ለመብቱ ትኩረት በመስጠት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

Related posts

June 13, 2023August 28, 2023 Event Update
በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት አተገባበር
July 7, 2023August 28, 2023 Press Release
በግንባታ የሥራ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታን ለማረጋገጥ የሕግና ፖሊሲ አተገባበሮችን ማሻሻል ያስፈልጋል
September 9, 2022October 6, 2022 Human Rights Concept
የሠራተኞች ሰብአዊ መብቶች
October 1, 2023October 1, 2023 Newsletter
EHRC in September 2023 | ኢሰመኮ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም.

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.