የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 9(3) እና 14(1) 

  • ሰዎች ሁሉ በፍርድ ቤቶችና በዳኝነት አካላት ፊት በእኩልነት ይታያሉ። ማንኛውም ሰው በቀረበበት የወንጀል ክስም ሆነ ስለ መብቶቹ እና ግዴታዎቹ በሚወሰንበት ማንኛውም ጉዳይ በሕግ በተቋቋመ፣ ሥልጣን ባለው፣ በነጻና ገለልተኛ የዳኝነት አካል ፍትሐዊ እና ግልጽ በሆነ ችሎት የመዳኘት መብት አለው። 
  • በወንጀል ክስ የተያዘ ወይም የታሰረ ሰው ከዳኛ ወይም በሕግ የመዳኘት ሥልጣን በተሰጠው አካል ዘንድ በአፋጣኝ ሊቀርብ ይገባል። ተገቢ በሆነ ጊዜ ውስጥም ዳኝነት የማግኘት ወይም የመለቀቅ መብት አለው።