የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባሕል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 7 (ሀ) (1)
- የዚህ ቃል ኪዳን ተዋዋይ ሀገራት እያንዳንዱ ሰው ፍትሐዊና አመቺ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት እንዳለው ዕውቅና ይሰጣሉ። በተለይም ይህ መብት ለሁለም ሠራተኞች ቢያንስ ምንም ዐይነት ልዩነት ሳይደረግ እኩል ዋጋ ላለው ሥራ ተገቢ እና እኩል ክፍያ፣ በተለይ ሴቶች ወንዶች ከሚሠሩበት ባላነሰ የሥራ ሁኔታ ውስጥ መሥራታቸውን እና ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ የሚያገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 42 (1) (መ)
- ሴቶች ሠራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው።