የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 30
- ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው።
የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 21
- በዴሞክራሲያዊ ሕብረተሰብ ውስጥ ለብሔራዊ ደኅንነት ወይም የሕዝብ ሰላምና ጸጥታ ጥቅም ፣ የሕዝብን ጤናና ሞራል ለመጠበቅ ወይም የሌሎችን መብቶችና ነፃነቶች ለማስከበር ከሚያስፈልገው እና በሕግ ከተደነገገው በቀር በዚህ መብት አጠቃቀም ላይ ምንም ዓይነት ገደብ አይደረግም።