የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 19 (2) እና የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 15 (1) (ሐ)
- ማንኛውም ሰው በሥነ-ጥበብ መልክ ሐሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብት አለው።
- አባል ሀገራት የማንኛውንም ሰው ከሥነ-ጽሑፋዊ ወይም ከሥነ-ጥበባዊ የሥራ ውጤቱ የሚመነጨውን የሞራል እና ቁሳዊ ጥቅም የማግኘት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ።
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 41 (9)
- መንግሥት የባህልና የታሪክ ቅርሶችን የመጠበቅ እና የመንከባከብ እንዲሁም ለሥነ-ጥበብ መስፋፋት አስተዋጽዖ የማድረግ ኃላፊነት አለበት።