የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 39 

  • ተዋዋይ ሀገራት የማናቸውም ዐይነት የእንክብካቤ እጦት፣ ብዝበዛ፣ ያልተገባ አያያዝ፣ ማሰቃየት ወይም ሌላ ማናቸውም ዐይነት ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ወይም ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት ወይም የትጥቅ ግጭት ሰለባ የሆነን ሕፃን በአካልና በሥነ ልቦና ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግምና ከኅብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል ለማድረግ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ።
  • ይህ ዐይነቱ ሕፃኑን ከጉዳቱ እንዲያገግም እና ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀል የማድረግ ተግባር የሕፃኑን ጤንነት፣ ለራስ ዋጋ የመስጠት ስሜት እና ክብር ለማዳበር በሚያመች ሁኔታ ውስጥ መከናወን አለበት።