የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 18 (2)
- ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው።
በሰዎች በተለይም በሴቶችና ሕፃናት የመነገድ ወንጀልን ለመከላከል፣ ለመግታትና ለመቅጣት የወጣ ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 3 (ሀ)
- በሰዎች መነገድ ማለት ሰዎችን በማስፈራራት ወይም ኃይል በመጠቀም ወይም በሌላ በማንኛውም ዐይነት መንገድ በማስገደድ፣ በመጥለፍ፣ በማጭበርበር፣ በማታለል፣ ሥልጣንን ወይም የተጎጂን ተጋላጭነት አላግባብ በመጠቀም፣ ወይም በሌላ ሰው ላይ ቁጥጥር ያለውን ሰው ፈቃድ ለማግኘት ክፍያ ወይም ጥቅማጥቅም በመስጠት ወይም በመቀበል ሰዎችን ለብዝበዛ ዐላማ የመመልመል፣ የማጓጓዝ፣ የማሸጋገር፣ የመቀበል ወይም የማስጠለል ድርጊት ነው።