የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 11
ማንኛውም ሰው በቂ ምግብ፣ ልብስና መኖሪያ ቤትን ጨምሮ ለራሱ እና ለቤተሰቡ በቂ በሆነ ደረጃ ለመኖር መብት አለው።
በቂ ምግብ የማግኘት መብት የሚከተሉት አራት ነጥቦችን ያካትታል
- በመጠንም ሆነ በጥራት ለሰው ልጅ በቂ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘትን፤
- ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ከብክለት የጸዳ ምግብ ማግኘትን፤
- በተጠቃሚው ባህል ተቀባይነት ያለው ምግብ ማግኘትን፤ እንዲሁም
- የምግብ ዘለቄታዊ ተደራሽነትን።